Posts

Showing posts from October, 2019

የክፍለ ከተማውን ሰላም በማረጋገጥ : ግጭቶችን በመፍታትና የሰላም እሴትን በመገንባት ጉልህ ሚና ለነበራቸው አካላት እውቅና ተሰጠ::

Image
የክፍለ ከተማውን ሰላም በማረጋገጥ : ግጭቶችን በመፍታትና የሰላም እሴትን በመገንባት ጉልህ ሚና ለነበራቸው አካላት እውቅና ተሰጠ:: ===================================== የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 9/2012 ዓ.ም) የየካ ክ/ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት በ2012 በጀት አመት ዝግጅት ምዕራፍ የክ/ከተማውን ጸጥታና ሰላም በማስጠበቅ : ግጭቶችን በመፍታት እና የሰላም እሴትን በመገንባት የላቀ ሚና ለነበራቸው ግለሰቦች እና ተቋማት እውቅና ሰጠ:: በእውቅና መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ የፀጥታ አባላት የህብረተሰቡን ሰላም በማስፈን ላደረጉት አስተዋፅኦ በአስተዳደሩ ስም አመስግነዋል:: የፀጥታ ሀይሎች የክፍለ ከተማውን ሰላም እና ጸጥታ የማስከበር ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም በተለይም ከህብረተሰቡ ጋር በመቀራረብ መንግስት የያዛቸው እቅዶች በውጤታማነት እንዲፈፀሙ ህገ መንግስቱንና ስርዓቱን ሊያስጠብቁ እንደሚገባ አቶ አስፋው አስምረውበታል:: አዲስ አበባ ከተማ ዓለምአቀፋዊ : አህጉራዊና ሀገራዊ መድረኮችን በሰላም እንድታስተናግድ የፀጥታ ሀይሉ ህዝቡን በማስተባበር ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ኮሚሽነር ፍስሐ ጋረደው ናቸው:: የፀጥታ ሀይሉ በተለመደው ትጋት የከተማዋን ሰላም ማስጠበቁን በቁርጠኝነት እንዲያስቀጥልም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል:: በዚህ የእውቅናና ሽልማት መድረክ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት : የፌደራል ፖሊስ : የአዲስ አበባ ፖሊስ : የክፍለ ከተማው የፀጥታ ሀይሎች አመራሮችና አባላት እንዲሁም የወረዳ አመራሮች በድምሩ ከ1500 በላ...

መልካ ቦሪ ኢሬቻ በዓል ከ46 ዓመት በኋላ በየካ ክ/ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ::

Image
መልካ ቦሪ ኢሬቻ በዓል ከ46 ዓመት በኋላ በየካ ክ/ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ:: ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 9/2012) በየካ ክፍለ ከተማ ወርዳ 14 በተለምዶ አባዶ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ከ46 አመት በፊት ሲከበር የነበረው የመልካ ቦሪ ኢሬቻ በዓል በኦሮሞ ህዝብ መሪነት ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን ተከብሯል፡፡ በበዓሉ ላይ የለገጣፎ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ :የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ: የክፍለ ከተማው የዲሞክራሲ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ዘመኑ ደሳለኝን ጨምሮ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች: አባ ገዳዎች: ቀሬና ቄሮች በመገኘት በዓሉን አክብረዋል። መልካ ቦሪ ኢሬቻ ተከብሮ በዋለ በሳምንቱ የሚከበር በዓል እንደሆነ እና በአባዶ አካባቢ ሲኖሩ የነበሩ የኦሮሞ ማህበረሰቦች ከክረምቱ የጨለማ ወራት ወደ በጋ ያሸጋገራቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት መሆኑን የወረዳ 14 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ እየሩስአሌም ግዛው ገልፀዋል:: የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ የእንኳን አደረሳችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ወ/ሮ ሀቢባ: አቶ ዘመኑ እና ወ/ሮ እየሩስአሌም በጋራ በመሆን ለበዓሉ የተዘጋጀውን ጩኮ ቆርሰዋል::

በህገወጥ መንገድ ባልተፈቀደ ቦታ ሲሸጥ የነበረ 183 ኩንታል ሲሚንቶ ተወረሰ።

Image
በህገወጥ መንገድ ባልተፈቀደ ቦታ ሲሸጥ የነበረ 183 ኩንታል ሲሚንቶ ተወረሰ። ========================= በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር በተለምዶ ሲሚንቶ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከተፈቀደላቸው ህጋዊ ቦታ ውጪ የእግረኛ መንገድ በመዝጋት ሲሚንቶ ሲሸጡ የነበሩ ነጋዴዎች ላይ በተወሰደ ኦፕሬሽን 183 ኩንታል ሲሚንቶ መውረሱን በክ/ከተማው ሰላምና ጸጥታ የደንብ ማስከበር ዘርፍ አስታውቋል። የደንብ ማስከበር ዘርፍ አስተባባሪ ኮ/ል ግርማ ደመቀ እንዳሉት ነጋዴዎቹ የሚፈፅሙት ተግባር ህገወጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ከድርጊታቸው ባለመቆጠባቸው ጥቅምት 7/2012 ዓ.ም የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከወረዳው ባለድርሻ አካላት እና ከጸጥታ ሀይል ጋር በወሰደው እርምጃ 183 ኩንታል ሲሚንቶ መውረሱንና ለመንግስት ገቢ ማድረጉን ገልጸዋል ሲል የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ ዘግቧል።

በ233 ህገወጥ ቤቶች ላይ ርምጃ መውሰዱን የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት አስታወቀ::

Image
በ233 ህገወጥ ቤቶች ላይ ርምጃ መውሰዱን የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት አስታወቀ:: ----------------------------------------- የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 6/2012 ዓ.ም) በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ካራ በሚባል አካባቢ ከወረዳውና የክፍለ ከተማው ፀጥታ ሀይል ጋር በመተባበር 233 ህገ ወጥ ቤቶችን ማፍረሱን የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት አስታወቀ:: የክፍለ ከተማው ሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ አያሌው እንዳሉት የፈረሱ ቤቶች ለበሬና በግ መገበያያ በተሰጠው ቦታ ላይ የተሰሩና ህገ ወጥ እርድና ምግብ ሲሰራባቸው የነበሩ ናቸው:: ህገ ወጥ እርድ መፈፀምና ለጤንነት አስጊ በሆነ ቦታ ምግብ አዘጋጅቶ ማቅረብ በሰው ጤና ላይ ከሚያመጣው ጠንቅ በተጨማሪ በህግ የተከለከለ ተግባር መሆኑ ይታወቃል::

የየካ ክፍለ ከተማ ባህል :ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ፅ/ቤት የአለም የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ የእውቅ እና ሽልማት በማዘጋጀት የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ::

Image
የየካ ክፍለ ከተማ ባህል :ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ፅ/ቤት የአለም የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ የእውቅ እና ሽልማት በማዘጋጀት የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ:: ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 6/2012) የክፍለ ከተማው ባህል :ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ፅ/ቤት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ 40ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ32 ጊዜ ሲከበር የቆየው የቱሪዝም ሳምንትን አስመልክቶ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ:: በፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ከተማ ባህል :ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የተዘጋጀ የቱሪዝም ጥናታዊ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰንዱ የቱሪዝም ትርጏሜ: የቱሪዝም አይነቶች: የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዋና ዋና አካላት: ከዘርፍ የተገኙ ጠቀሜታዎችና በከተማው ቱሪዝም ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶች ተዳሰዋል:: የቀረበውን ሰነድ መሰረት በማድረግ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በአዲ አበባ ከተማ ያልተጎበኙ በረካታ ቅርሶች መኖራቸውን በመጥቀስ በተቀናጀ መልኩ መጎብኘት እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል:: የቱሪዝም ቀንን ችግኝ በመንከባከብ: ጉብኝት በማድረግ እና ሲፖዝየም በማዘጋጀት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ 3 ወረዳዎች የእውቅና ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በክረምት መረሀ- ግብር የኪነ-ጥበብ ስልጠና ለወሰዱ ግለሰቦችና ስልጠናውን ለሰጡ አካላት በክፍለ ከተማው አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ በአቶ አለሙ ኢብሮ አማካኝነት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል::

ለስደት ተጋላጭ ለሆኑ 47 ወጣቶች የስራ ፈጠራ ስልጠና መስጠቱን የየካ ክፍለ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ገለፀ::

Image
ለስደት ተጋላጭ ለሆኑ 47 ወጣቶች የስራ ፈጠራ ስልጠና መስጠቱን የየካ ክፍለ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ገለፀ:: --------------------------------------- የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 6/2012 ዓ.ም) የየካ ክፍለ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ፕላን ኢንተርናሽናል ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ለስደት ተጋላጭ ለሆኑ 47 ወጣቶች ለ7 ተከታታይ ቀናት በስራ ፈጠራ ዙሪያ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልፇል:: እንደ ፅ/ቤቱ ገለፃ ወጣቶቹ የስራ እቅድ አውጥተው እና ተደራጅተው ወደስራ የሚገቡ ሲሆን በሰሩት እቅድ መሰረት ፕላን ኢንተርናሽናል የመነሻ ካፒታል ነፃ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ተነግሯል:: ሰልጣኞቹ በበኩላቸው የወሰዱት ስልጠና በህይወታቸው : በስራ ሰአት አጠቃቀማቸው : ችግሮችን እንዴት መሻገር እንደሚቻልና በንግድ ስራቸው ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል መሆኑን ገልፀው ህጋዊ ሰውነት ለማግኘት በሚያደርጉት እንቅስቃሴና በመስሪያ ቦታ በኩል ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል ተናግረዋል:: የፅ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ ማያ ታደሰ ወጣቶቹ ስራ ፈላጊ መሆናቸው ተረጋግጦ የተመለመሉት በስራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ፅ/ቤት በኩል እንደሆነና በፍጥነት ወደስራ እንዲገቡ ከአዲስ ካፒታልና ሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል:: ወጣቶቹ ህጋዊ እውቅና ካገኙ በሗላ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ወደስራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል::

የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት አስታወቀ::

Image
እድሜያቸው 14 አመት ላልሞላቸው በሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤት ለሚማሩ ልጃ ገረዶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት አስታወቀ:: --------------------------------------------- የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 6/2012 ዓ.ም) የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት ከጥቅምት 10-14/2012 ድረስ እድሚያቸው 14 አመት ከ9-14 ለሆኑ ልጃ ገረዶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል:: ክትባቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ የገለፀው ፅ/ቤቱ በሁሉም 1ኛና 2ኛ ደረጃ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የክትባት ዘመቻው ይካሄዳል ብሏል:: የክፍለ ከተማው ነዋሪም ሆነ የትምህርት ማህበረሰብ በዚህ ክትባት ሁሉም ልጃ ገረዶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲያደርግ ፅ/ቤቱ ጥሪውን አስተላልፏል:: በዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ የካንሰር በሽታ ገዳይነት ምጣኔ 4 በመቶ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በማህፀን ካንሰር ቫይረስ 24 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች ተጋላጭ ናቸው:: በኢትዮጵያ በየዓመቱ 7000 ያህል ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር ሲያዙ ከእነዚህ ውስጥ 5000 ያህሉ እንደሚሞቱ ጥናቱ ያመለክታል:: የማህፀን በር ካንሰር መንስኤው human papilloma virus/HPV/ የሚባል በግብረ ስጋ ግንኙነት በቀላሉ የሚተላለፍ ቫይረስ ሲሆን ሁለቱንም ፆታዎች እንደሚያጠቃና በወንዶች የመራቢያ አካል ኪንታሮት (genital wart) የሚባለውን በሽታ ሲያመጣ ሴቶች ላይ ግን የማህፀን በር ካንሰርን ያስከትላል::

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ

Image
የነጥብ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ ------------------------------------- ትርጉም 1. «የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ» ማለት የአንድን ሠራተኛ ደመወዝ ወደ አዲሱ የደመወዝ ስኬል ለማሸጋገር ሲባል ቅርበቱ እየታየ የነበረውን ደመወዝ እንደሁኔታው ወደ አዲሱ የደመወዝ ስኬል የመነሻ፣ የእርከን ወይም የጣሪያ ደመወዝ ላይ ለማሳረፍ የሚፈቅድ የደመወዝ ማስተካከያ ነው። 2. የመሸጋገሪያ ደመወዝ» ማለት በዚህ መመሪያ አንቀጽ 5 ንዑስ አንቀጽ 3 (ለ) መሠረት አንድ ሠራተኛ በደመወዝ ስኬል ሽግግሩ የሚያገኘውን የደመወዝ ስኬል መሸጋገሪያ መጠን ለሶስት በማካፈል መደበኛ ደመወዙ ላይ ጨምሮ እስከ ሰኔ ወር 2013 ዓ.ም. ድረስ የሚከፈል ደመወዝ ነው፡፡ የመመሪያው የተፈጻሚነት ወሰን ----------------------------- ይህ መመሪያ ተግባራዊ የሚደረገው የሥራ መደቦቻቸው በነጥብ የሥራ ምዘና ዘዴ ተመዝነው ደረጃ በወጣላቸው የሥራ መደቦች ላይ ለተደለደሉ ሠራተኞች ብቻ ነው፡፡ ልዩ ልዩ ውሳኔዎች ----------------------- 1) በሥራ ላይ የሚውለው የደመወዝ ስኬል የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት እና የመንግስት የመክፈል አቅም ከግምት ውስጥ ገብቶ የተቀረጸውና በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተወሰነውና በከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በፀደቀው መሰረት የደመወዝ ስኬል በሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተግባራዊ ይሆናል፡፡ /የዚህ መመሪያ አባሪ ሆኖ ተያይዟል፡፡ 2) ወደፊት ልዩ የደመወዝ ስኬል የማይፈቀድ ስለመሆኑ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት በሀገር አቀፍ ደረጃ መተግበርን ተከትሎ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ያሉ የደመወዝ ስኬሎችን ወደ አንድ የማሰባሰብ ተግባርና ሥርዓቱ ዘላ...

ጌጅ ኮሌጅ ለህዝባዊ ሰራዊት አፀደ ህፃናት ት/ቤት የወንበርና ጠረጴዛ ድጋፍ አደረገ::

Image
ጌጅ ኮሌጅ ለህዝባዊ ሰራዊት አፀደ ህፃናት ት/ቤት የወንበርና ጠረጴዛ ድጋፍ አደረገ:: ------------------------------------------- የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 5/2012 ዓ.ም) ጌጅ ኮሌጅ ለህዝባዊ ሰራዊት አፀደ ህፃናት ትምህርት ቤት 100 መቀመጫ ወንበርና 25 ጠረጴዛ ድጋፍ አደረገ:: የኮሌጁ ፕሬዝዳንት አቶ ሞገስ ሲሳይ መንግስት በትምህርት ስራ ላይ እያደረገ ያለውን በጎ ተግባር የማገዝ ግዴታ ስላለብን ድጋፉን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል:: ኮሌጁ ከዚህ በፊት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ አይዘነጋም:: ለችግረኞችና ለመንግስት ሰራተኞች በዝቅተኛ ክፍያና በነፃ የትምህርት እድል ድጋፍ በማድረግ በትምህርት ዘርፍ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነም ተነግሯል:: የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዮት ድንቁ በ2012 በጀት አመት ለትምህርት ስራው የመንግስትን ስራ በማገዝ ባለሀብቶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑን ገልፀው ኮሌጁ ላደረገው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል:: የትምህርት ቤቶችን የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለመፍታት የክፍለ ከተማው ወተመህ ተወካዮች ባለሀብቶችን በማስተባበር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ::

በመማሪያ ክፍል ጥበትና መምህራን እጥረት ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየተፈጠረ መሆኑን የጣፎ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገለፀ::

Image
- በመማሪያ ክፍል ጥበትና መምህራን እጥረት ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየተፈጠረ መሆኑን የጣፎ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገለፀ:: - የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም የምገባ ፕሮግራም ያልጀመሩ የአባዶና ጣፎ ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል:: -------------------------------------- የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 4/2012 ዓ.ም) በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የጣፎ መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመማሪያ ክፍል ጥበት : የመምህራን እጥረት : የውሐና መብራት መቆራረጥ : የምግብ ማብሰያና መመገቢያ አዳራሽ : የአጥር እንዲሁም የግቢ ማስፋፊያ ችግር እንዳለበት አስታወቀ:: ትምህርት ቤቱ 4650 ተማሪዎችን መዝግቦ ትምህርት ቢጀምርም የተማሪ ቁጥር ከመማሪያ ክፍል ጋር አለመጣጣሙን ገልፇል:: በትምህርት ቤቱ የተማሪ ክፍል ጥምርታ ለኬጂ 1 ለ 105 : ለ1ኛ ደረጃ ደግሞ 1 ለ 70 መሆኑን ተመልክተናል:: በትምህርት ቤቱ የተማሪዎች ምገባ ያልተጀመረበትን ምክንያት እንዲያብራራ ተጠይቆ የማብሰያ ችግር አለብኝ ብሏል:: ምገባውን ለማድረግ የተደራጁ ሴቶች ብድር እንዳልተመቻቸላቸውና በራሳቸው አቅም ምገባ ማስጀመር እንደማይችሉ ተናግረዋል:: የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ ጥያቄው ተደራጅቶ ለአስተዳደሩ እንዳልቀረበ ጠቅሰው የመሰረተ ልማት : የአጥርና ማስፋፊያ ጥያቄ በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ ተናግረዋል:: ከክፍል ጥበት ጋር የተያያዘው ችግር ተጨማሪ ክፍሎች እስኪገነቡ መማር ማስተማሩን በፈረቃ በማድረግ ት/ቤቱ ሊፈታ እንደሚገባው አቅጣጫ ተቀምጧል:: በየካ ወረዳ 14 አባዶ የመ...

The 21st Health Conference was held at Entoto no.2 Health Center.

Image
The 21st Health Conference was held at Entoto no.2 Health Center. ---------------------------------- Yeka Social Media (October 3, 2012) Due to the National Health Summit being held under the theme 'Multi-level Cooperation for a Healthy and Prosperous Country', the sub-City Health Office has been honored with a number of programs at Entoto Health Center. A report on the implementation of the PHC's was presented to professionals from all regions and the Health Bureau. Experts from across the region visited the implementation of the Family Health Care Unit. Delegates raised questions about professional migration and shortages, continuity of the program, access to an ambulance service and the promotion system. Addis Ababa Health Bureau, for its part, said I am working to maintain the Family Health Unit program as a permanent system. During the implementation of this program, the focus on accessibility of the service has been emphasized in addressing problem-...

21ኛው የጤና ጉባኤ በእንጦጦ ቁጥር 2 ጤና ጣቢያ ተካሔደ::

Image
21ኛው የጤና ጉባኤ በእንጦጦ ቁጥር 2 ጤና ጣቢያ ተካሔደ:: ----------------------------------- የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 3/2012 ዓ.ም) 'ዘርፈ ብዙ ትብብር ለጤናማና የበለፀገች ሐገር' በሚል መሪ ቃል እየተካሔደ ያለውን ሀገር አቀፍ የጤና ጉባኤ ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት በእንጦጦ ቁጥር 2 ጤና ጣቢያ በተለያዩ ፕሮግራሞች ተከብሯል:: በጉባኤው የቤተሰብ ጤና ክብካቤ አሀድ (PHC) ትግበራ ሪፖርት ከሁሉም ክልሎችና ከጤና ቢሮ ለተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል:: ከክልል የመጡ የልምድ ልውውጥ ልዑካን የቤተሰብ ጤና ክብካቤ አሀድ አተገባበር ሁኔታን ጎብኝተዋል:: ልዑካን በባለሙያ ፍልሰትና እጥረት : በፕሮግራሙ ቀጣይነት : በአንቡላንስ አገልግሎት ተደራሽነትና በማበረታቻ ስርዓት ዙሪያ ጥያቄ አንስተዋል:: የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በበኩሉ የቤተሰብ ጤና አሀድ ፕሮግራም ዘላቂ ስርዓት ሆኖ እንዲቀጥል እየሰራሁ ነው ብሏል:: በዚህ ፕሮግራም ትግበራ ወቅት ከባለሙያ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በየጊዜው በመፍታት በአገልግሎቱ ተደራሽነት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነም ተብራርቷል:: ከ50 በላይ ከአፍሪካና ከሀገር ውስጥ የተውጣጡ የጤና ተቋማት ባለሙያዎች በጤና ጣቢያው ተገኝተው የቤተሰብ ጤና አሀድ ትግበራ ልምድ ወስደዋል:: እንጦጦ ቁጥር 2 ጤና ጣቢያ በ90 የጤና ባለሙያዎች ለ40,262 የህብረተሰብ ክፍሎች በ5 የቤተሰብ ጤና ቡድኖች የቤተሰብ ጤና አገልግሎትን ፕሮግራምን መተግበር ከጀመራ 4 አመታትን አስቆጥሯል::

ሰንደቅ አላማ = የሐገራዊ አንድነት ምልክት

Image
ሰንደቅ አላማ = የሐገራዊ አንድነት ምልክት ============================ ሰንደቅ አላማ የሚለው መጠሪያ ከሁለት ቃላት የተገኘ ነው፡፡ ይህም “ሰንደቅ” እና ”አላማ” ከሚሉ ቃላት የተመሰረተ ሲሆን የቃላቱ የተናጥል ትርጉም፡ - ሰንደቅ፡- ማለት ምርኩዝ፣ ምሰሶ፣ በትር ማለት ሲሆን - ዓላማ፡- ማለት ምልክት፣ አቋም፣ ስብስብ እንዲሁም የነፃነት፣ የሉዓላዊነት ምልክት ማለት ነው፡፡ የሁለቱ ቃላት ጥምረት “ሰንደቅ ዓላማ” የሚለው ቃል በአንድ ላይ የአገር መታወቂያ፣ የሕዝብ አንድነት መጠበቂያ እንዲሁም የክብር መለያ ምልክት የሚለውን ትርጉም የሚሰጥ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሰንደቅ ዓላማ የአንድ ህዝብንና መንግስት ሉዐላዊነት፣ ስልጣንና ነፃነት ምልክት ወይም ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ ሰንደቅ አላማ የአገር እና የህዝብ ምልክት ነው፡፡ ሰንደቅ አላማ የሃገር ምልክት በመሆኑ ከሰንደቅ ዓላማው ፊት በቆመ ቁጥር የሃገሩ ምስል የማይከሰትበት ዜጋ የለም፡፡ ከአለም ታሪክ እንደምንረዳው ሃገራትና ዜጎች ከቅኝ ግዛት ተፅዕኖ ሲላቀቁ መጀመሪያ ከፍ አድርገው የሚያሳዩት ሰንደቅ አላማቸውን ነው፡፡ ህዝቦችና አገራት በሰላም አደባባይም ሆነ በጦር ሜዳ ዉሎ ለድል ሲበቁ ቅድሚያ የሚሰቅሉት ሰንደቅ አላማቸውን ነው፡፡ ይህን በማድረግም ፍቅርና ክብራቸውን እጅግ ከፍ ባለ መልኩ ለሰንደቅ አላማቸው ይገልፃሉ፡፡ ይህ ማለት ህዝቦች በአንድ ሰንደቅ አላማ ስር በመሰባሰብ ሉዓላዊነታቸውን ይገልፃሉ፡፡ ሰንደቃችን ጥቁሮችን ነጻ ያወጣች ፡ የድላችን አርማ ነች። ብዙዎች ደም አፍስሰው አጥንት ከስክሰው ሐገር አቁመውባታል፡፡ አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ልምላሜያችንን ተስፋችንንና ድል አድራጊነታችንን የምንገልጽበት አርማችን ነው። ያለ ሰን...

መሰረተ የካ ህብረት ስራ ዩኒየን 5 ሚልዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ገለፀ::

Image
መሰረተ የካ ህብረት ስራ ዩኒየን 5 ሚልዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ገለፀ:: ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ (የካ ማህበራዊ ሚዲያ ጥቅምት 2/2012) መሰረተ የካ ህብረት ስራ ዮኒየን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል:: በጉባዬው የ2011 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2012 በጀት አመት እቅድን በተመለከተ ከህብረት ስራ ዮኒየን አመራሮች ጋር ገምግሟል:: በ2011 ከ59 ተቋማት ጋር ውል በመፈፀም 199 አይነት ምርቶችን ማቅረብ መቻሉን: በዓላትን ምክንያት በማድረግና 6ኛው ሀገር አቀፍ ባዛርና ኤግዝብሽን ማዘጋጀት መቻሉ: ከመሰረታዊ ማህበራት ጋር መድረኮችን በመፍጠር ግንኙነቱን ማጠናከር እና ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ :የግብርና ምርቶች አቅርቦት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱና ለክረምት የሚሆን 5000 ኩንታል ጤፍ ክምችት መያዝ መጀመሩ: ለበዓላት ዶሮ: እንቁላል: ቅቤ: አይቤ እና የስጋ በሬ በማቅረብ ገብያ ማረጋጋት መቻሉን በሪፖቱ አቅርቧል:: በበጀት አመቱ የተገኙ የገቢና የወጪ አፈፃፀም ከኢንዱስትሪና ከግብርና ምርት ሽያጭ 146,342,236.02 ብር እና ከማዳበሪያና ከካርቶን ሽያጭ 20,613.00 ገቢ መገኘቱን በሌላ በኩል በቆጠራ 2,155,507.19 ብር : በግዥ 138,970,773.42 ብር: ጠቅላላ ለሽያጭ የቀረበ 141,126,280.61 ብር እና አስተዳደራዊ ወጪ 1,880,447.19 ብር ማውጣቱን በኦዲት ሪፖርት አቅርቧል:: ከጉባኤው ተሳታፊዎች ለበአል ተገዝተው የተሰራጩ የዶሮና በሬ ግዢ ግልፀኝነት : ከኦዲት ግኝት ሪፖርት እና ከቦርድ አመራርነት በራሳቸው ፍቃድ ስለለቀቁ አባል ጥያቄዎችን አንስተዋል:: ለተነሱ ጥያቄዎች የየካ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ መለሰ ጋሻው ዩኒየኑ...

* 25, 535, 419.40 Birr government cost could be saved by the 17th voluntary service

Image
* 25, 535, 419.40 Birr government cost could be saved by the 17th voluntary service, Yeka sub-city's youth and sports office said. * Winter volunteer service program has officially launched today. -------------------------------------------- Yeka Social Media (October 2, 2012) The sub-City of Yeka administration has announced its winter volunteer service that has been running in various program today. According to Dereje Terebo, head of the Sub-city's Youth and Sports Office, 1019 students benefited from the training of basic computer and 6319 students benefited from tutoring program in the summer. According to the 17th Summer Volunteer Services Report, 552 thousands of seedlings have been planted by 161,141 residents involvement . With a participation of 32,228 residents, 1422 m3 of garbage was cleared, and 21,100 dozen notebooks: 28881 pens: 18332 pencils were collected and distributed. The New Year's Gift for 2487 Infants: New Year's Gift of 899,195 Bir...

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሎ የበጋ በጎ ተግባር መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል::

Image
* በ17ኛው በጎ ፈቃድ አገልግሎት 25 ሚሊዮን 535 ሽህ 419.40 ብር የመንግስት ወጪ ማስቀረት እንደተቻለ የየካ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት አስታወቀ:: * የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሎ የበጋ በጎ ተግባር መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል:: -------------------------------------------- የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 2/2012) የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ዘርፎች ሲያካሂድ የቆየውን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር በዛሬው እለት አጠናቆ የበጋ በጎ ተግባር መርሐ ግብሩን ይፋ አድርጏል:: በክረምቱ መርሐ ግብር በማጠናከሪያ ትምህርት በ200 በጎ ፈቃደኞች 6319 : በመሰረታዊ ኮምፒውተር ስልጠና በ34 አሰልጣኞችን በማሳተፍ 1015 ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደረጀ ተሬቦ ተናግረዋል:: በ17ኛው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሪፖርት መሰረት 161,141 ነዋሪዎችን በማሳተፍ 552 ሽህ ችግኞች ተተክለዋል:: 32,228 ነዋሪዎችን በማሳተፍ 1422 ሜ/ኩ ቆሻሻ የተፀዳ ሲሆን ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች 21,100 ደርዘን ደብተር : 28881 ፍሬ እስክብሪቶ : 18332 እርሳስ ተሰብስቦ ተሰራጭቷል:: ለ2487 አቅመ ደካሞች 899,195 ብር የሚገመት የአዲስ አመት ስጦታ : ከጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኘ ድጋፍ 100 ሽህ ብር በማሰባሰብ ለኩላሊት ህሙማን ማህበር መበርከቱንም ሪፖርቱ ያመለክታል:: 4400 በጎ ፈቃደኞች ደም መለገሳቸውንና የ207 አቅመ ደካማ ቤቶች መታደሳቸውንም አቶ ደረጀ አውስተዋል:: 251 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በትራፊክ ደህንነት ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ ሲሆን  ለ5670 ነዋሪዎች...

ህዳሴ ግድበ 2011

Image

በኢሬቻ ዙሪያ የህዝብ ውይይት ተደረገ::

Image
* ህ ብረተሰቡ የኢሬቻ በዓል እንግዶችን በፍቅር ተቀብሎ በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንዲሸኝ ጥሪ ቀረበ:: *ለመዲናችን አዲስ አበባ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል:: *በአሉን ለማክበር ከተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ከ10 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ወደመዲናዋ ይመጣል:: *************************************** በኢሬቻ በአል ምንነትና አከባበር ስነ ስርዓት ዙሪያ ከተለያዩ የህብረተሰቦች ክፍሎች ጋር በየካ ክፍለ ከተማ የፖናል ውይይት ተደርጏል:: ህብረተሰቡ የበዓሉን እንግዶች በፍቅር ተቀብሎ በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንዲሸኝ ጥሪ ቀርቧል:: ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ከክረምት ወራት ወደ ብርሐን ላሸጋገረው ዋቃ(አምላክ) ምስጋና የሚያቀርብበት : ህዝቡ አንድነቱን የሚያጠናክርበት : ባህሉንና ስርዓቱን የሚያስተዋውቅበት : የፖለቲካ የሀይማኖትና ሌላ አስተሳሰብ ሳይገድበው በጋራ የሚሰባሰብበት የገዳ ስርዓት አካል መሆኑ ተገልፇል:: በአሉ በአመት 2 ጊዜ በክረምት ወራት ማጠናቀቂያና በበጋ ወራት መጨረሻ በጋራ ይከበራል:: የመጀመሪያው ኢሬቻ ቢራ የተሰኘው በአል በወንዝ አካባቢ በክረምት ወራት መጨረሻ የፊታችን መስከረም 24 የሚከበር ሲሆን ኢሬቻ አርፋሳ ደግሞ በበጋው ማጠናቀቂያ ወቅት በተራራ አካባቢ ይከበራል ተብሏል:: በአዲስ አበባ በሚከበረው ኢሬቻ ከመላው ኦሮሚያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል:: በአሉ ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑንና ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደሚያስገኝ ነው የተገለፀው::

በኢሬቻ የማንኛውም ፓርቲ ባንዲራ መያዘ ተከለከለ::

Image
በኢሬቻ በዓል የማንኛውም ፓርቲ ባንዲራና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ፅሁፎችን ያዘሉ ቲሸርቶችና ህትመቶች ይዞ መግባት እንደማይቻል ተገለፀ :: የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ ሀይሎችና ከህዝብ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት ተደርጏል :: ______________________________________________ ( መስከረም 21/2012) የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኢሬቻ በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፖሊሶችና የህዝብ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት አድርጏል :: ከበዓሉ አርማ ውጪ የማንኛውም ፓርቲ ባንዲራ ይዞ መሳተፍ እንደማይቻልና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ የህትመት ውጤቶችን መጠቀም ክልክል መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል :: በዓሉን ለፖለቲካ ፍጆታ ለመጠቀና የበዓሉን ገፅታ ለማጠልሸት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራ መሆኑን አስተዳደሩ ገምግሟል :: ህብረተሰቡና የበዓሉ ተሳታፊም የነዚህ ርካሽ ፖለቲከኞች አላማ እንዳይሳካ እንዲያደርግና ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል :: በክፍለ ከተማው ከ 50 ሽህ በላይ ህዝብ በዓሉ በሰላም በሚጠናቀቅበት ሁኔታ ምክክር መደረጉንና የበዓሉን ሰላም ለማረጋገጥ ለ 1500 በበጎ ፈቃደኝነት ፍተሻ የሚያደርጉ ፎሌዎች ስምሪት መስጠቱን አስተዳደሩ ገልፇል ::  ክፍለ ከተማው እንግዶች ከሚገቡባቸው በሮች አንዱ እንደመሆኑ ጥብቅ ፍተሻና ክትትል እንደሚደረግና በበዓሉ ዕለት ከላምበረት መነኻሪ ጀምሮ ወደመኻል ከተማ የትራፊክ እንቅስቃሴ አይኖርም ተብሏል ::