የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሎ የበጋ በጎ ተግባር መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል::

* በ17ኛው በጎ ፈቃድ አገልግሎት 25 ሚሊዮን 535 ሽህ 419.40 ብር የመንግስት ወጪ ማስቀረት እንደተቻለ የየካ ክፍለ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት አስታወቀ::

* የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጠቃሎ የበጋ በጎ ተግባር መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል::
--------------------------------------------
የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 2/2012)

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ዘርፎች ሲያካሂድ የቆየውን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር በዛሬው እለት አጠናቆ የበጋ በጎ ተግባር መርሐ ግብሩን ይፋ አድርጏል::

በክረምቱ መርሐ ግብር በማጠናከሪያ ትምህርት በ200 በጎ ፈቃደኞች 6319 : በመሰረታዊ ኮምፒውተር ስልጠና በ34 አሰልጣኞችን በማሳተፍ 1015 ተማሪዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ደረጀ ተሬቦ ተናግረዋል::

በ17ኛው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሪፖርት መሰረት 161,141 ነዋሪዎችን በማሳተፍ 552 ሽህ ችግኞች ተተክለዋል:: 32,228 ነዋሪዎችን በማሳተፍ 1422 ሜ/ኩ ቆሻሻ የተፀዳ ሲሆን ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች 21,100 ደርዘን ደብተር : 28881 ፍሬ እስክብሪቶ : 18332 እርሳስ ተሰብስቦ ተሰራጭቷል:: ለ2487 አቅመ ደካሞች 899,195 ብር የሚገመት የአዲስ አመት ስጦታ : ከጤና ባለሙያዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች በተገኘ ድጋፍ 100 ሽህ ብር በማሰባሰብ ለኩላሊት ህሙማን ማህበር መበርከቱንም ሪፖርቱ ያመለክታል::

4400 በጎ ፈቃደኞች ደም መለገሳቸውንና የ207 አቅመ ደካማ ቤቶች መታደሳቸውንም አቶ ደረጀ አውስተዋል:: 251 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በትራፊክ ደህንነት ስራ ላይ ተሰማርተው የቆዩ ሲሆን  ለ5670 ነዋሪዎች በኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ ግንዛቤ ተፈጥሯል:: በቲያትር ስክሪፕት 125 : በአማተር የኪነ ጥበብ ሙያ 163 : በስፖርትና መዝናኛ 4447 : በፀረ ዶፒንግ 4230 : በሰልፍ ዲፌንስ  1500: በስፖርት ጨዋነት 2500 ወጣቶች ስልጠና ወስደዋል ነው የተባለው::

በአጠቃላይ 221,092 ነዋሪዎችን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሳተፉ በማድረግና 35,755 ነዋሪዎችን ተጠቃሚ በማድረግ 25 ሚሊዮን 535 ሽህ 419.40 የመንግስት ወጪ ማዳን መቻሉ ተነግሯል::

በ2012 የበጋ በጎ ፈቃድ መርሀ ግብር በደም ልገሳ 3000 ሰዎች ለማሳተፍ : በነፃ ህክምና 1000 አቅመ ደካሞችን ለማገዝ : 33000 ችግኞች ለመንከባከብ : በፅዳት ዘመቻ 140 ሽህ ህዝብ ለማነቃነቅ : 250 ወጣቶች በትራፊክ ደህንነት ለማሰማራት እና 4200 ዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ያሉ አቅመ ደካሞችን ለመደገፍ እቅድ መያዙ ተገልፇል::

በበጋ በጎ ተግባር መርሐ ግብር መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ በዚህ በጎ ተግባር ንቁ ተሳትፎ ያደረጉ አካላትን አመስግነው በጎነት ለራስ እንደመሆኑ የተጀመረው መልካም ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል::

በክረምት በጎ ፈቃድ ጥሩ አፈፃፀም ለነበራቸው ተቋማት : ወጣቶችና በጎ ፈቃደኞች የሰርተፍኬትና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::

ዘጋቢ : ሁናቸው ጌትነት





Comments

Popular posts from this blog

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ