Posts

Showing posts from July, 2019

ለ2012 የስራ ዘመን 1.9 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዟል

Image
ክፍለ ከተማው ለ 2012 የስራ ዘመን 1 ቢሊየን 942 ሚሊዮን 901 ሽህ 384 ብር በጀት መመደቡን አስታወቀ :: ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ የየካ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ፅ / ቤት የ 2012 የስራ ዘመን በጀትን አስመልክቶ ከምክር ቤት ዘርፍ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደገለፀው ለአስተዳደሩ የስራ ማስኬጃና ካፒታል በጀት 1.9 ቢሊዮን ብር መመደቡን አስታውቋል :: ከተመደበው በጀት 90% የሚሆነው ከገቢና አገልግሎት ክፍያ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚሰበሰብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በ 2012 በጀት አመት 977.9 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱ ታውቋል :: ለማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ማለትም ለጤናና ትምህርት የበጀት አፈፃፀማቸውንና  የማስፈፀም አቅማቸውን መሰረት ያደረገ ከፍተኛ በጀት መያዙ ታውቋል :: ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ክፍት የስራ መደቦች 50 ሚሊዮን እንዲሁም 20 ሚሊዮን መጠባበቂያ በጀት መያዙንም ፅ / ቤቱ አስታውቋል :: በ 2012 የተያዘው በጀት ከአምናው ተመሳሳይ ዘመን ጋር ሲነፃፀር የ 334238612 ወይም የ 20.76% ብልጫ እንዳለው ተጠቅሷል :: የምክር ቤት ዘርፍ ኮሚቴዎች በበኩላቸው በገቢ ግብር መሰብሰብ ተግባር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል ::

በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጠ፡፡

Image
  “ህገ-ወጥ የሠዎች ዝውውር ወንጀልን መከላከል የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው፡፡”   ህጋዊ የሰዎች ዝውውር የስራ ኃይል ወደ ውጭ ሃገር በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ፣ የስራ አጥነት ችግርን ለመቀነስ ፣ የላቀ ቴክኖሎጂንና እውቀትን ለማሸጋገር እና የአገር ውስጥ ምርትን ወደ ውጭ ለመላክ የጎላ ጥቅም ቢኖረውም ህገ-ወጥ ሲሆን ግን በዜጎችና በሐገር ገፅታ ላይ የከፋ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል፡፡ የየካ ክ/ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ፣ ለአረጋውያን ፣ ለወጣትና ሴት አደረጃጀት አመራሮች በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ሰዎን በህገ ወጥ መንገድ የማዘዋወር ወንጀል ሰዎችን በማስፈራራት ፤ ሀይልን ወይም ሌላ ዓይነት መንገድን በመጠቀም በጠለፋ ፣ በማታለል ፣ በማሳሳት ፣ ስልጣንን ወይም የሰዎችን ለወንጀሉ ተጋላጭነት በመጠቀም የሚፈፀም ህገወጥ ድርጊት መሆኑ በመድረኩ ተብራርቷል፡፡ ድህነተ ፣ ስራ አጥነትና የተሸለ ህይወት ፍለጋ የህገ ወጥ ዝውውር ምክንያች በመሆናቸው በነዚህ ችግሮች ዙሪያ መስራት እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል፡፡ ህብረተሰቡም የህገ-ወጥ ድርጊት ፈጻሚ አካላትን ማለትም ህገ-ወጥ ደላሎችን ፣ ህገ-ወጥ ድርጊት የሚፈፅሙ ህጋዊ ሽፋን ያላቸው ሰራተኛና ስራ አገናኝ ኤጀንሲዎችንና የንግድ ድርጅቶችን በጋራ መዋጋት ይኖርበታል ተብሏል፡፡ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም  በመንግስት በኩል ተገቢውን አደረጃጀትና ቅንጅት መፍጠር ፣ ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ስራዎችን መስራት እና ህጋዊ የውጭ ሃገር ስራ ስምሪት አገልግሎትን ቀልጣፋና ውጤታማ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የስልጠና ሰነዱ ያስረዳል፡፡

በትምህርት ጥራት ዙሪያ ለዘርፉ ባለድርሻዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡

Image
የየካ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት  በትምህርት ጥራት ዙሪያ ለዘርፉ ባለድርሻዎች ስልጠና ሰጠ፡፡ የየካ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በትምህርት ጥራት ዙሪያ ለግልና መንግስት ትምህርት ቤቶች መምህራንና ርዕሳነ መምህራን ፣ ለወረዳ የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች እዲሁም ለዘርፉ ባለድርሻ አካላት በትምህርት ጥራት ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡