ለ2012 የስራ ዘመን 1.9 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዟል

ክፍለ ከተማው 2012 የስራ ዘመን 1 ቢሊየን 942 ሚሊዮን 901 ሽህ 384 ብር በጀት መመደቡን አስታወቀ::
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
የየካ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ /ቤት 2012 የስራ ዘመን በጀትን አስመልክቶ ከምክር ቤት ዘርፍ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደገለፀው ለአስተዳደሩ የስራ ማስኬጃና ካፒታል በጀት 1.9 ቢሊዮን ብር መመደቡን አስታውቋል::



ከተመደበው በጀት 90% የሚሆነው ከገቢና አገልግሎት ክፍያ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚሰበሰብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን 2012 በጀት አመት 977.9 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱ ታውቋል::

ለማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ማለትም ለጤናና ትምህርት የበጀት አፈፃፀማቸውንና የማስፈፀም አቅማቸውን መሰረት ያደረገ ከፍተኛ በጀት መያዙ ታውቋል::

ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ክፍት የስራ መደቦች 50 ሚሊዮን እንዲሁም 20 ሚሊዮን መጠባበቂያ በጀት መያዙንም /ቤቱ አስታውቋል::


2012 የተያዘው በጀት ከአምናው ተመሳሳይ ዘመን ጋር ሲነፃፀር 334238612 ወይም 20.76% ብልጫ እንዳለው ተጠቅሷል:: የምክር ቤት ዘርፍ ኮሚቴዎች በበኩላቸው በገቢ ግብር መሰብሰብ ተግባር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል::

Comments

Popular posts from this blog

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ

በዜሮ ዓመት የወጣ ክፍት የስራ ማስታወቂያ

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት