Posts

Showing posts from April, 2020

የኮቪድ 19 አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብ

Image
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ማስፈጸሚያ ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 3/2012 አንቀፅ 4/1/ መሰረት የሚከተለውን ማስፈጸሚያ ደንብ አውጥቷል:: 1. አጭር ርእስ ይህ ደንብ ‘‘ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ማስፈፀሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር——–/2012’’ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል:: 2. ትርጓሜ 1. ‘‘አዋጅ’’ ማለት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ነው፤ 2. ‘‘የሚኒስትሮች ኮሚቴ’’ ማለት በዚህ ደንብ አንቀፅ 5 የተቋቋመው ኮሚቴ ማለት ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ፣ በኮሚቴው የሚቋቋሙና ውክልና የሚሰጣቸው በፌዴራል፣ በክልሎች፣ በከተማና በወረዳ ደረጃ ያሉ ንዑሳን ኮሚቴዎችንም ያካትታል፤ 3. ‘‘ስብሰባ’’ ማለት ማንኛውንም ተግባር ለመፈጸም፣ ለመነጋገር፣ ለመወያየት ወይም መሰል ተግባራትን ለማከናወን የአንድ ቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጪ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ በአንድ ቦታ በአካል መገኘት ነው፤ 4. “ኳራንታይን” ማለት በኮቪድ-19 ተይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎችን በቫይረሱ መያዝ አለመያዛቸው እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ ቦታ እንዲቆዩ ማድረግ ነው፤ 5. “ለይቶ ማቆየት” ማለት በኮቪድ-19 መያዙ የተረጋገጠ ሰው ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳያስተላልፍ ከቫይረስ ነፃ እስኪሆን ድረስ ለብቻው ለይቶ እንዲቆይ ማድረግ ነው፤ 6. “ሀገር አቀፍ የህዝብ ትራንስፖርት” ማለት ከአንድ ክልል ከተማ ወደሌላ ክልል ከተማ የሚደረግ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሲሆን በአንድ ክልል ውስጥ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ የሚደረግ የህዝብ ትራንስፖርትንም ያ