Posts

የኮቪድ 19 አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብ

Image
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ማስፈጸሚያ ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 3/2012 አንቀፅ 4/1/ መሰረት የሚከተለውን ማስፈጸሚያ ደንብ አውጥቷል:: 1. አጭር ርእስ ይህ ደንብ ‘‘ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ማስፈፀሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር——–/2012’’ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል:: 2. ትርጓሜ 1. ‘‘አዋጅ’’ ማለት የኮቪድ-19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 3/2012 ነው፤ 2. ‘‘የሚኒስትሮች ኮሚቴ’’ ማለት በዚህ ደንብ አንቀፅ 5 የተቋቋመው ኮሚቴ ማለት ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ፣ በኮሚቴው የሚቋቋሙና ውክልና የሚሰጣቸው በፌዴራል፣ በክልሎች፣ በከተማና በወረዳ ደረጃ ያሉ ንዑሳን ኮሚቴዎችንም ያካትታል፤ 3. ‘‘ስብሰባ’’ ማለት ማንኛውንም ተግባር ለመፈጸም፣ ለመነጋገር፣ ለመወያየት ወይም መሰል ተግባራትን ለማከናወን የአንድ ቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጪ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ በአንድ ቦታ በአካል መገኘት ነው፤ 4. “ኳራንታይን” ማለት በኮቪድ-19 ተይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎችን በቫይረሱ መያዝ አለመያዛቸው እስኪረጋገጥ ድረስ በተለየ ቦታ እንዲቆዩ ማድረግ ነው፤ 5. “ለይቶ ማቆየት” ማለት በኮቪድ-19 መያዙ የተረጋገጠ ሰው ቫይረሱን ወደ ሌሎች ሰዎች እንዳያስተላልፍ ከቫይረስ ነፃ እስኪሆን ድረስ ለብቻው ለይቶ እንዲቆይ ማድረግ ነው፤ 6. “ሀገር አቀፍ የህዝብ ትራንስፖርት” ማለት ከአንድ ክልል ከተማ ወደሌላ ክልል ከተማ የሚደረግ ማንኛውም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሲሆን በአንድ ክልል ውስጥ ከአንድ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ የሚደረግ የህዝብ ትራንስፖርትንም ያ

Vacancy Anouncement

#Vacancy_Announcement 1.Zero Experience 2.Commercial Bank of Ethiopia 3. share for your friends To get updates of Yeka Mahiberawi Media, Follow our page, inviite your friends. --------------------------------------------------------------------- Fresh graduates' job: Bank Trainees Job Description: The Commercial Bank of Ethiopia would like to invite qualified and interested candidates for the following position. Position: Bank Trainee Place of work: Branches under Addis Ababa area District (East, West, South and North) and outlying Districts (Bahir Dar, Dire Dawa, Shashemene, Adama, Jimma, Gondar, Hawassa, Mekelle, Nekemte, Wolaita Sodo and Dessie) Educational Qualification: BA Degree in Economics, Management or Accounting or other business related fields recognized university. Work Experience: Not required ( zero year) CGPA: 2.5 and above Year of Graduation: 2010 and 2011 Ethiopian Calendar Age: 35 and Below 35 Salary: As per the Bank’s salary scale

ኮሮና ቫይረስ ምንድነው?

Image
ኮሮና ቫይረስ ምንድነው? የኮሮና ቫይረስ ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን ሞትን ሊያስከትል የሚችል ህመም ነው።  የ ቫይረሱ  መተላለፊያ መንገዶች በሽታው ያለበት ሰው ሲያስነጥስ፣ ባልበሰሉ ምግቦች፣ ከታማሚው ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ ይተላለፋሉ። የበሽታው ምልክቶች በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥ እና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል። በሽታው የጠናባቸው ሰዎች ላይ ደግሞ እንደ የሳምባ ምች እና ከባድ የመተንፈሻ አካላት ህመም ይስተዋላል።  በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ምን ማድረግ አለባቸው? ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ካለብዎ ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የጤና ተቋም ይሂዱ። የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገራት ሄደው ከነበረም ይህንንም ለጤና ባለሙያ ያሳውቁ። በሚያስሉበት እና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት ይሸፍኑ። አፍን አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃ እና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል።  በበሽታው መያዝዎን ሪፖርት ለማድረግ በነጻ የስልክ መስመር 8335 ወይም የመደበኛ ስልክ 0112765340 መጠቀም ይችላሉ። በሽታው ወዳለባቸው ሃገራት ሲጓዙ ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች ትኩሳት እና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ከፈጠሩ እጅን በሳሙናና ውሃ መታጠብ  ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋጽኦዎችን አለመመገብ  በሕይወት ካሉም ሆነ ከሞቱ የቤት እ
Image
ክፍት የስራ መደቦች ለስራ ፈላጊ የገፃችን ተከታታዮች   ታህሳስ 2/2012 የወጡ የኢትዮጵያ ብዝሐ ህይወት ኢንስቲቲዩት 89 ክፍት ቦታዎች ( 49- ቦታዎች 0 ልምድ , 40- ልምድ የሚጠይቁ ) የመመዝገቢያ ቦታ ቀበና ኬንያ ኢንባሲ ጎን የመመዝገቢያ ቀን ከትላንት ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፌደራል ስፖርት ኮሚሽን (Federal Sport Commission ) 15 ክፍት መደቦች ( 6- ቦታዎች 0 ዓመት , 9- ቦታዎች በልምድ የመመዝገቢያ ቦታ መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት የመመዝገቢያ ጊዜ ከትላንት ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ( Ethiopian Ministry of Revenues ) 10 ቦታዎች (  with EXP): የመመዝገቢያ ቦታ መገናኛ ዋናው መስሪያ ቤት ( ከትላንት ጀምሮ ባሉት 6 ተከታታይ የስራ ቀናት ለበለጠ መረጃ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታህሳስ 2/2012 እትም መመልከት ይቻላል :: የመረጃ ምንጫችን ethiopage.com ነው yekasec.blogspot.com የጡመራ ገፃችን ለእናንተ አዳዲስ መረጃዎችን ያደርሳል ::

የኩላሊት ጠጠር

Image
የኩላሊት ጠጠር ምንድን ነው? -------------------- ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የየካ ማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ተከታዮች ዋናው ጤና በሚል አምድ የተለያዩ የጤና ጉዳዮችን የሚዳስሱ አርዕስት በመምረጥና መረጃ በማሰባሰብ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል:: ለዛሬ ስለ ኩላሊት ጠጠረ ምንነት: መንስኤው: ምልክቱ: ህክምናውና መከላከያ ዘዴው የሚዳስስ ፁሁፍ መርጠንሎታል መልካም ንባብ ይሁንልዎ! የኩላሊት ጠጠር የሚባለው በኩላሊት ውስጥ የጠጣር ነገሮች መጋገር ወይም መሰብሰብ ሲሆን የጠጣር ነገሮቹም ምንጭ በሽንት ውስጥ የሚገኙ የምግብ ንጥረ ነገሮች ናቸው:: የኩላሊት ጠጠሮች በተለያየ መልኩ ሊከፈሉ ይችላሉ፤ ከነዚህም ውስጥ በሚገኙበት ቦታ ማለትም በሽንት ትቦና በሽንት ፊኛ፤ በጠጠሮቹ ውስጥ በሚገኙ ማእድናት ማለትም ካልሺየም፣ማግኒዢየምና አሞኒየም ፎስፌት፤ የሽንት አሲድ ወይም ሌላ ማእድናት የያዙ በማለት ሊሆን ይችላል። የኩላሊት ጠጠር የከፍተኛ ህመም ምንጭ ሲሆን በአብዛኛው ወንዶችን ያጠቃል፤ ወንዶች በአብዛኛው የኩላሊት ጠጠር ህመም ከ30-40 ባለው እድሜያቸው ሲጀምራቸው ሴቶች ላይ ግን ዘግይቶ ሊከሰት ይችላል። የኩላሊት ጠጠሮች አብዛኛውን ጊዜ ምንም የህመም ስሜትና ጉዳት ሳያስከትሉ በሽንት መስመር ውስጥ አልፈው ከሰውነት ይወገዳሉ:: ነገር ግን ጠጠሮቹ በመጠን ከጨመሩ ማለትም ከ3 ሚ.ሜ አካባቢ ከደረሱ፣ የሽንት ትቦን ሊዘጉ ይችላሉ:: የሽንት ትቦ በጠጠር መዘጋት ሽንት በቀላሉ እንዳይተላለፍ (ፓስቴርናል አዞቶሚያ) ብሎም ሽንት ወደ ኋላ በመመለስና በኩላሊት ውስጥ በመከማቸት (ሃይድሮኔፕሮሊስ) ጉዳት ሊያደርስ ይችላል:: ይሄ የጤና ችግር (ሃይድሮኔፕሮሊስ) ከታችኛው የጎድን አጥንት አንስቶ እስከ የዳሌ አጥንት ድረስ ባለው ቦታ፣ በብሽሽትና በታችኛው የምግብ መ

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 Federal Civil Servants Proclamation 1064-2017 በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚካሄደውን የምልመላና መረጣ ሥርዓትን በመሰረታዊነት በመለወጥና በአገር አቀፍ ደረጃ የሙያና የሥራ ብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት በመዘርጋት፣ እንዲሁም የመንግስት ሠራተኛው በዚህ ሥርዓት ውስጥ እንዲያልፍ በማድረግ ብዝሀነትን ያረጋገጠና ሀገሪቱ እያስመዘገበች ያለችውን እድገት ለማስቀጠል የሚያስችል ፐብሊክ ሰርቪስ ለመገንባትና የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም በሰው ሃብት ሥራ አመራር ረገድ ያመጣቸውን ውጤቶች ለማጎልበትና ለማስቀጠል የሚያስችል ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ያሉ ሰራተኞችን ወጥነት ባለው መልኩ ለመምራትና እውቀታቸውንና ችሎታቸውን በተገቢው ሁኔታ ለመጠቀም የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ያሏቸውን ሠራተኞች በማቆየትና አዳዲስ ሰራተኞችን በመሳብ ተወዳዳሪ ለመሆን እንዲችሉ የተሻሻሉ የሥራ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጅዋል፡፡ ክፍል አንድ ጠቅላላ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ትርጓሜ የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፣ 1/    “የመንግሥት ሠራተኛ” ማለት በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው፤ ሆኖም የሚከተሉትን አይጨምርም፤ ሀ) ሚኒስትር ዴኤታዎችን፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችን፣ እንዲሁም በተመሣሣይ ደ