የኩላሊት ጠጠር
የኩላሊት ጠጠር ምንድን ነው?
--------------------
ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የየካ ማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ተከታዮች ዋናው ጤና በሚል አምድ የተለያዩ የጤና ጉዳዮችን የሚዳስሱ አርዕስት በመምረጥና መረጃ በማሰባሰብ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል:: ለዛሬ ስለ ኩላሊት ጠጠረ ምንነት: መንስኤው: ምልክቱ: ህክምናውና መከላከያ ዘዴው የሚዳስስ ፁሁፍ መርጠንሎታል መልካም ንባብ ይሁንልዎ!
የኩላሊት ጠጠር የሚባለው በኩላሊት ውስጥ የጠጣር ነገሮች መጋገር ወይም መሰብሰብ ሲሆን የጠጣር ነገሮቹም ምንጭ በሽንት ውስጥ የሚገኙ የምግብ ንጥረ ነገሮች ናቸው:: የኩላሊት ጠጠሮች በተለያየ መልኩ ሊከፈሉ ይችላሉ፤ ከነዚህም ውስጥ በሚገኙበት ቦታ ማለትም በሽንት ትቦና በሽንት ፊኛ፤ በጠጠሮቹ ውስጥ በሚገኙ ማእድናት ማለትም ካልሺየም፣ማግኒዢየምና አሞኒየም ፎስፌት፤ የሽንት አሲድ ወይም ሌላ ማእድናት የያዙ በማለት ሊሆን ይችላል።
የኩላሊት ጠጠር የከፍተኛ ህመም ምንጭ ሲሆን በአብዛኛው ወንዶችን ያጠቃል፤ ወንዶች በአብዛኛው የኩላሊት ጠጠር ህመም ከ30-40 ባለው እድሜያቸው ሲጀምራቸው ሴቶች ላይ ግን ዘግይቶ ሊከሰት ይችላል። የኩላሊት ጠጠሮች አብዛኛውን ጊዜ ምንም የህመም ስሜትና ጉዳት ሳያስከትሉ በሽንት መስመር ውስጥ አልፈው ከሰውነት ይወገዳሉ::
ነገር ግን ጠጠሮቹ በመጠን ከጨመሩ ማለትም ከ3 ሚ.ሜ አካባቢ ከደረሱ፣ የሽንት ትቦን ሊዘጉ ይችላሉ:: የሽንት ትቦ በጠጠር መዘጋት ሽንት በቀላሉ እንዳይተላለፍ (ፓስቴርናል አዞቶሚያ) ብሎም ሽንት ወደ ኋላ በመመለስና በኩላሊት ውስጥ በመከማቸት (ሃይድሮኔፕሮሊስ) ጉዳት ሊያደርስ ይችላል:: ይሄ የጤና ችግር (ሃይድሮኔፕሮሊስ) ከታችኛው የጎድን አጥንት አንስቶ እስከ የዳሌ አጥንት ድረስ ባለው ቦታ፣ በብሽሽትና በታችኛው የምግብ መፍጫ ክፍሎች አካባቢ ለህመም ስሜት ይዳርጋል::
መንስኤዎች
------------
ለኩላሊት ጠጠር መፈጠር ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ የአመጋገብ ልማድ፣ ውኃ በበቂ አለመጠጣት፣ ከፍተኛ የሆነ የእንስሳት ሥጋ (ፕሮቲን) መመገብ፣ ጨው በብዛት መጠቀም፣ የስኳር ምርቶች፣ የፍራፍሬ ስኳር (ፍሩክቶስ)፣ ኦክሳሌት የያዙ ምግቦች (ኦክሳሌት በብዙ ዕፅዋት ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ሲሆን በተለይም በሰባ ዶሮ፣ በጥቁር አዝሙድ፣ በብላክ ፒፐር፣ ፐርስሊ፣ ስፒናች፣ ካካዎ፣ ቸኮላት፣ ኦቾሎኒ፣ አብዛኛዎቹ እንጆሬዎች ውስጥ ይገኛል)፣ ለስላሳ መጠጦች ናቸው።
የህመሙ ምልክቶች
------------------
በአብዛኛውን ጊዜ የኩላሊት ጠጠሮች በኩላሊትዎ ውስጥ ካልተዘዋወሩ አሊያም ወደ ዩሬተር(ሽንትን ከኩላሊትዎ ወደ ፊኛ የሚወስደው ቱቦ) ካልወረዱ በስተቀር ምንም አይነት የህመም ምልክት አያሳዩም። ስለሆነም የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ።
• ጎንና ጀርባዎ ላይ ከፍተኛ ህመም መኖር
• ወደ ታችኛው የሆድዎ ክፍልና ብሽሽት የሚሰራጭ ህመም መፈጠር
• ሽንት ሲሸኑ ህመም መኖር
• ቀይ ወይም ቡናማ የመሰለ የሽንት መልክ መከሰት
• ጉም የመሰለ ወይም ሽታ ያለው ሽንት መውጣት
• ማቅለሽለሽና ማስታወክ
• በተደጋጋሚ ለመሽናት መፈለግ
• ከተለመደው ጊዜ/ብዛት በላይ ሽንት መሽናት
• ኢንፌክሽን ካለ ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት መኖርና
• በጣም ትንሽ መጠን ያለው ሽንት መሽናት ናቸው።
በኩላሊት ጠጠር ምክንያት የሚከሰተው ህመም ሊለዋወጥ ይችላል። ለምሳሌ ጠጠሩ ወደ ሌላ ቦታ ከሄደ/ ከተዘዋወረ ህመሙ ሊጨምር ይችላል።
የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?
የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ካሉ የህክምና ባለሙያዎን ባስቸኳይ ያማክሩ።
• ህመሙ በጣም ከፍተኛ ከሆነና መቀመጥ ያለመቻል ወይም ምቾት የሚሳንዎ ከሆነ
• ህመሙን ተከትሎ ማቅለሽለሽና ትውከት ከመጣ
• ከህመሙ ጋር ትኩሳትና ብርድ ብርድ ማለት ካለ
• ከሽንትዎ ጋር ደም ከመጣ
• ሽንትዎን መሽናት ከተቸገሩ
ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች
-----------------------
• በዚህ በፊት በቤተሰብዎ ወይም በራስዎ ላይ መሰል ችግር ከነበረ
• የፈሳሽ እጥረት/ ድርቀት ካለ፡- በየቀኑ ፈሳሽ በበቂ መጠን መውሰድ ካልቻሉ ለኩላሊት ጠጠር ይጋለጣሉ። ከሌሎቹ ይልቅ በሞቃታማ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩና ከመጠን ያለፈ ላብ የሚያልባቸው ሰዎች ለችግሩ ተጋላጭ ናቸው።
• የተወሰኑ የምግብ አይነቶች፡- የፕሮቲን፣ የሶዲየምና የስኳር ይዘታቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦችን የሚያዘወትሩ ሰዎች ለተወሰኑ የኩላሊት ጠጠር አይነቶች ይጋለጣሉ።
• ውፍረት፡- ከመጠን ያለፈ ክብደት ያላቸው ሰዎች ላይ የኩላሊት ጠጠር የመፈጠሩ ጉዳይ ከፍተኛ ነው።
የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር መከላከል
የኩላሊት ጠጠር እንዳይፈጠር ለመከላከል የአኗኗር ዘይቤ ለውጥና መድሃኒቶች ከፍተኛውን ሚና ይጫወታሉ።
• በየቀኑ በቂ ፈሳሽ/ውሃ መጠጣት፡- ሞቃታማና ደረቅ የአየር ንብረት ውስጥ የሚኖሩ ከሆነ ወይም በመደበኛ ሁኔታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ከሆነ ሽንት በበቂ መጠን እንዲመረት/ እንዲወጣ ፈሳሽ በበቂ መጠን መጠጣት ይመከራል። ሽንትዎ ነጣ ያለና ንፁህ ከሆነ ውሃ በበቂ መጠን እየወሰዱ መሆኑን ያሳያል።
• መጠነኛ የኦክዛሌት/ oxalate ይዘት ያላቸውን የምግብ አይነቶች ማዘውተር፡- የካልሲየም ኦግዛሌት ድንጋይ እየተፈጠረ ካለ ወይም ተጋላጭነት ካለዎ እንደ ስኳር ድንች፣ ቆስጣ፣ ኦቾሎኒ፣ ሻይ፣ ቼኮሌት፣ የአኩሪ አተር ተዋፅኦዎችና ቀይስር ያሉ ምግቦች መመገብ ያስፈልጋል።
• የጨውና የፕሮቲን ይዘታቸው አነስተኛ የሆኑ ምግቦችን መምረጥ/ማዘውተር፡- የሚመገቡትን የጨው መጠን መመጠን እንዲሁም ከእንስሳት ተዋፅኦ ውጪ ያሉ የፕሮቲን ምንጮችን መመገብ (ለምሳሌ ባቄላና አተር)
• የካልሲየም ይዘታቸው ከፍ ያለ ወይም በካልሲያም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ነገር ግን የካልሲየም ሰፕሊመንት (ተጨማሪ እንክብል) ሲወስዱ ጥንቃቄ ያድርጉ፡- በካልሲየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ የኩላሊት ጠጠር የመፈጠር እድሉን አይጨምሩትም። የህክምና ባለሙያዎ ካልከለከለዎ በስተቀር የካልሲየም ይዘታቸው ከፍ ያሉ ምግቦችን መመገብ ይቀጥሉ። ነገር ግን የካልሲየም ሰፕልመንቶች ከኩላሊት ጠጠር መከሰት ጋር ተያያዥት/ግንኙነት ስላላቸው ከመውሰድዎ በፊት የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ።
ምርመራና ሕክምና
---------------
የኩላሊት ጠጠር መኖር በሰውነት አቋም ምርመራዎች፣ በበሽታ ምልክቶች መኖር፣ በሽንት ምርመራ፣ በራጅ ምርመራ እንዲሁም በበሽተኛው የበፊት የጤና ምርመራ ውጤቶች ድጋፍ ሊታወቅ ይችላል:: የአልትራሳውንድ እና የደም ምርመራዎችም የኩላሊት ጠጠር በሽታ መኖሩን ለማወቅ ያስችላሉ::
የኩላሊት ጠጠር ህመም ካላስከተለ የሰውነትን ሁኔታ እየገመገሙ በጥንቃቄ መጠበቅ ጥሩ አማራጭ ሊሆን ይችላል:: ህመም ለሚያስከትል የኩላሊት ጠጠር በሽታ የመጀመሪያ እርዳታ ህመሙን መቆጣጠር መሆን አለበት:: ለዚህ ሁኔታ ጥቅም ላይ የሚውሉ መድኃኒቶችን ሐኪም በማማከር መውሰድ ይቻላል:: ከፍተኛ የሆነ የኩላሊት ጉዳት ወይም ህመም ከተከሰተ ግን የቀዶ ጥገና አስፈላጊ ሊሆን ይችላል:: ለምሳሌ፣ አንዳንድ ጠጠሮች በነዛሪ የሞገድ ረብሻ(ሾክ ዌቭ) አማካኝነት ወደ ጥቃቅን ጠጠሮች በመሰባበር በሽንት እንዲወገዱ ማድረግ ሲቻል፣ በአንዳንድ ሁኔታ ደግሞ ቀዶ ጥገናዎች አስፈላጊ ሊሆኑ ይችላሉ::
አንዳንድ ጊዜም በሽንት መሽኛ ትቦ ውስጥ ሌላ ሰው ሰራሽ ትቦ (ዩሬትራል ስቴንት) በመቀጠል በጠጠር የተዘጋውን ቦታ ወደ ጎን አልፎ እንዲሄድ በማድረግ የህመም ስሜቱን መቀነስ ይቻላል::
የመከላከያ መንገዶች
----------------
የኩላሊት ጠጠርን ለመከላከል የሚደረጉ ጥረቶች በታማሚው ውስጥ በሚገኘው የኩላሊት ጠጠር አይነት (የማዕድን ይዘት) ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። የአመጋገብ ስልት በኩላሊት ጠጠር መፈጠር (መከማቸት) ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርግ ይችላል።
የኩላሊት ጠጠርን መፈጠርን መከላከል ወይም መቀነስ የሚቻለው የአመጋገብ ሥልትን በማስተካከልና በሽንት ውስጥ የሚገኙ ለኩላሊት ጠጠር መከማቸት መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ የማእድናትን መጠን ለመቀነስ የሚረዱ መድኃኒቶችን በመጠቀም ነው። የሕክምናው የሚከተሉትን የአመጋገብ ሥልቶችን መከተል የኩላሊት ጠጠርን ለመቀነስ እንደሚረዳ ይመከራል፡-
• ሲትሬት (በሎሚና በብርቱካን ውስጥ የሚገኝ አሲድ ነው) ያላቸውን ፈሳሾች በብዛት መጠጣት፣ የፈሳሽ አወሣሠዱም በብዛትና በቀን እስከ ሁለት ሊትር የሽንት መጠን እስኪደርስ ቢሆን ይመከራል። በዚህ መንገድ የሽንትን ፒ.ኤች5 አካባቢ በማድረግ በተለይ በሽንት አሲድ (ዩሪክ አሲድ) ምክንያት የሚመጡ ጠጠሮችን ለማስወገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል።
• የካልሺየም አወሳሰድ መጠንን ከ 1000- 1200 ሚ.ግ መጠን በቀን ውስጥ ከፍ ማድረግ፤
• የሶዲየም አወሳሰድ መጠንን ከ 2300 ሚ.ግ በቀን በታች እንዲሆን ማድረግ፤
• የቪታሚን ሲ የቀን ፍጆታን ከ 1000 ሚ.ግ በቀን በታች እንዲሆን ማድረግ፤
• የእንስሳት ፕሮቲን (ሥጋና ስብን) መቆጣጠርና፤
• ኦክሳሌት የያዙ ምግቦችን (ከላይ ተጠቅሰዋል) መቀነስ ናቸው።
መረጃውን ያገኘነው ከኢትዮዽያ ፕረስ ድርጅት የፌስ ቡክ ገፅ ላይ ነው::

Comments
Post a Comment