Posts

Showing posts from November, 2019

መጤ የባህል ወረርሽኝ ከየት ወደዬት?

Image
የአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ ጥናት ------------------------------------------ “ የጥናት ቡድኑ አስራ ሁለት የሚሆኑ የቀን ጭፈራ ቤቶችን ለመመልከት የበቃ ሲሆን ከጭፈራ በተጨማሪም ሲጋራ ማጨስ ፣መሳሳም ... ጥንድ ጥንድ እየሆኑ ወደጉዋሮ በመውጣት ለወሲብ ክፍሎችን መከራየት ... በወንበር ፣በአግዳሚ ወንበር፣ ሶፋ፣ መሬት ... ምንም ቦታ ሳይመርጡ ኃላፊነት በጎደለው መልኩ የየራሳቸውን ስሜት ለማርካት ወሲብ ይፈጽማሉ፡፡ በጭፈራ ቤቶች አካባቢ መኪና ውስጥ ጫት ይዘው የሚቀመጡ ወንዶች ሴት ሕጻናቶቹ ከጭፈራው ቤት ሲወጡ ጠብቀው ለወሲብ አገልግሎት ይዘዋቸው ይሄዳሉ ” አቶ ስንታየሁ ደመቀ ... የጥናቱ አስተባባሪ  መጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች ... በወጣቶችና ሰቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ለይቶ ለማወቅ እንዲረዳን ተገቢው እርምጃ በሚመለከታቸው አካላት ሁሉ እንዲወሰድ ለማስቻል የአዲስ አበባ ሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ከሌሎች ከሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር ጥናት አድርጎ ይፋ አድርጎአል፡፡ በዚህ እትም የለሊት እና የእራቁት ጭፈራ ቤቶችን የማሳጅ አገልግሎትን እንደሽፋን በመጠቀም የሚሰሩ የወሲብ መስተንግዶዎችን እንዲሁም የጫት መቃሚያና ሽሻ ማጨሻ ቤቶችን ተግባር ታነቡ ዘንድ እነሆ ብለናል፡፡ ምንጫችን አቶ ስንታየሁ ደመቀ በአዲስ አበባ ሴቶችና ሕጻናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ወጣቶችን የማሳተፍና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ ስራ መሪ እና የጥናቱ

የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣ ረቂቅ አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣ ረቂቅ አዋጅ ------------------------------ መግቢያ ሰብዓዊ ክብርን የሚገረስሱ እና ሆን ተብሎ የሚሰራጩ ሃሰተኛ ንግግሮችን በሕግ መከልከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኝቱ፤ የጥላቻ ንግግርና የሃስተኛ መረጃ ስርጭት የሚያስከትሉት ግጭትና ጉዳት ለእኩልነት፣ለሰላም፣ ለዲሞክራሲና ለሕዝቦች አንድነት ትልቅ ጠንቅ በመሆኑ፤ መሰረታዊ መብቶች ላይ የሚጣሉ ገደቦች በሕግ የተደነገጉ፣ በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውን አላማ ለማስፈጸም የሚወጡና ተመጣጣኝ መሆን እንዳለባቸው በመገንዘብ፤ በኢትዮጲያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት እንቀፅ 55(1) መሰረት የሚከተለው ታውጇል፡፡ ክፍል አንድ አጠቃላይ 1. አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የጥላቻ ንግግርንና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከል የወጣ አዋጅ ቁጥር .../2012“  ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ 2. ትርጉም የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካለሆነ በቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ - 1. “ ንግግር ” ማለት በቃል፣ በጽሑፍ፣ በምሥልና ሥዕል፣ በቅርጻ ቅርጽ እና በሌሎች ተመሳሳይ መንገዶች መልእክትን የማስተላለፍ ተግባር ነዉ፡፡ 2. “ የጥላቻ ንግግር ” ማለት የሌላን ግለሰብን፤ የተወሰነ ቡድንን ወይም ማህበረሰብን ብሄርን፤ ሀይማኖትን፤ ቀለምን፤ ጾታን፤ አካል ጉዳተኝነትን፤ ዜግነትን፤ ስደተኝነትን፤ ቋንቋን