በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና ተሰጠ፡፡

 “ህገ-ወጥ የሠዎች ዝውውር ወንጀልን መከላከል የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት ነው፡፡” 





ህጋዊ የሰዎች ዝውውር የስራ ኃይል ወደ ውጭ ሃገር በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ፣ የስራ አጥነት ችግርን ለመቀነስ ፣ የላቀ ቴክኖሎጂንና እውቀትን ለማሸጋገር እና የአገር ውስጥ ምርትን ወደ ውጭ ለመላክ የጎላ ጥቅም ቢኖረውም ህገ-ወጥ ሲሆን ግን በዜጎችና በሐገር ገፅታ ላይ የከፋ ጠባሳ ጥሎ ያልፋል፡፡

የየካ ክ/ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ፣ ለአረጋውያን ፣ ለወጣትና ሴት አደረጃጀት አመራሮች በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ሰዎን በህገ ወጥ መንገድ የማዘዋወር ወንጀል ሰዎችን በማስፈራራት ፤ ሀይልን ወይም ሌላ ዓይነት መንገድን በመጠቀም በጠለፋ ፣ በማታለል ፣ በማሳሳት ፣ ስልጣንን ወይም የሰዎችን ለወንጀሉ ተጋላጭነት በመጠቀም የሚፈፀም ህገወጥ ድርጊት መሆኑ በመድረኩ ተብራርቷል፡፡


ድህነተ ፣ ስራ አጥነትና የተሸለ ህይወት ፍለጋ የህገ ወጥ ዝውውር ምክንያች በመሆናቸው በነዚህ ችግሮች ዙሪያ መስራት እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል፡፡ ህብረተሰቡም የህገ-ወጥ ድርጊት ፈጻሚ አካላትን ማለትም ህገ-ወጥ ደላሎችን ፣ ህገ-ወጥ ድርጊት የሚፈፅሙ ህጋዊ ሽፋን ያላቸው ሰራተኛና ስራ አገናኝ ኤጀንሲዎችንና የንግድ ድርጅቶችን በጋራ መዋጋት ይኖርበታል ተብሏል፡፡ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታትም  በመንግስት በኩል ተገቢውን አደረጃጀትና ቅንጅት መፍጠር ፣ ተከታታይነት ያላቸው የግንዛቤ ስራዎችን መስራት እና ህጋዊ የውጭ ሃገር ስራ ስምሪት አገልግሎትን ቀልጣፋና ውጤታማ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የስልጠና ሰነዱ ያስረዳል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት