የክፍለ ከተማውን ሰላም በማረጋገጥ : ግጭቶችን በመፍታትና የሰላም እሴትን በመገንባት ጉልህ ሚና ለነበራቸው አካላት እውቅና ተሰጠ::

የክፍለ ከተማውን ሰላም በማረጋገጥ : ግጭቶችን በመፍታትና የሰላም እሴትን በመገንባት ጉልህ ሚና ለነበራቸው አካላት እውቅና ተሰጠ::=====================================

የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 9/2012 ዓ.ም)
Image may contain: 22 people, crowd and indoor
የየካ ክ/ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ፅ/ቤት በ2012 በጀት አመት ዝግጅት ምዕራፍ የክ/ከተማውን ጸጥታና ሰላም በማስጠበቅ : ግጭቶችን በመፍታት እና የሰላም እሴትን በመገንባት የላቀ ሚና ለነበራቸው ግለሰቦች እና ተቋማት እውቅና ሰጠ::
በእውቅና መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ የፀጥታ አባላት የህብረተሰቡን ሰላም በማስፈን ላደረጉት አስተዋፅኦ በአስተዳደሩ ስም አመስግነዋል:: የፀጥታ ሀይሎች የክፍለ ከተማውን ሰላም እና ጸጥታ የማስከበር ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም በተለይም ከህብረተሰቡ ጋር በመቀራረብ መንግስት የያዛቸው እቅዶች በውጤታማነት እንዲፈፀሙ ህገ መንግስቱንና ስርዓቱን ሊያስጠብቁ እንደሚገባ አቶ አስፋው አስምረውበታል::
Image may contain: 16 people, crowd
አዲስ አበባ ከተማ ዓለምአቀፋዊ : አህጉራዊና ሀገራዊ መድረኮችን በሰላም እንድታስተናግድ የፀጥታ ሀይሉ ህዝቡን በማስተባበር ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ያሉት ደግሞ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ኮሚሽነር ፍስሐ ጋረደው ናቸው:: የፀጥታ ሀይሉ በተለመደው ትጋት የከተማዋን ሰላም ማስጠበቁን በቁርጠኝነት እንዲያስቀጥልም ኮሚሽነሩ ጥሪ አቅርበዋል::
Image may contain: 1 person, standing and indoor
በዚህ የእውቅናና ሽልማት መድረክ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት : የፌደራል ፖሊስ : የአዲስ አበባ ፖሊስ : የክፍለ ከተማው የፀጥታ ሀይሎች አመራሮችና አባላት እንዲሁም የወረዳ አመራሮች በድምሩ ከ1500 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል:: በበጀት አመቱ በመጀመሪያው ሩብ የስራ ዘመን በሰላምና ፀጥታው ዘርፍ አመርቂ ውጤት ላስመዘገቡ : ለሰላም ሲሉ የአካል ጥቃት ለተፈፀመባቸው እና በብቃት በመምራት ተልዕኳቸውን በአግባቡ ለተወጡ አካላት እውቅና በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል::
Image may contain: 13 people, crowd

Comments

Popular posts from this blog

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ