መልካ ቦሪ ኢሬቻ በዓል ከ46 ዓመት በኋላ በየካ ክ/ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ::

መልካ ቦሪ ኢሬቻ በዓል ከ46 ዓመት በኋላ በየካ ክ/ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ::~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 9/2012)
Image may contain: 2 people, people smiling, people standing, crowd, flower and outdoor
በየካ ክፍለ ከተማ ወርዳ 14 በተለምዶ አባዶ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ከ46 አመት በፊት ሲከበር የነበረው የመልካ ቦሪ ኢሬቻ በዓል በኦሮሞ ህዝብ መሪነት ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን ተከብሯል፡፡
በበዓሉ ላይ የለገጣፎ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ :የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ: የክፍለ ከተማው የዲሞክራሲ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ ዘመኑ ደሳለኝን ጨምሮ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ አመራሮች: አባ ገዳዎች: ቀሬና ቄሮች በመገኘት በዓሉን አክብረዋል።
Image may contain: 12 people, people smiling, people standing and outdoor
መልካ ቦሪ ኢሬቻ ተከብሮ በዋለ በሳምንቱ የሚከበር በዓል እንደሆነ እና በአባዶ አካባቢ ሲኖሩ የነበሩ የኦሮሞ ማህበረሰቦች ከክረምቱ የጨለማ ወራት ወደ በጋ ያሸጋገራቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት መሆኑን የወረዳ 14 ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ እየሩስአሌም ግዛው ገልፀዋል::
የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ የእንኳን አደረሳችሁ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ወ/ሮ ሀቢባ: አቶ ዘመኑ እና ወ/ሮ እየሩስአሌም በጋራ በመሆን ለበዓሉ የተዘጋጀውን ጩኮ ቆርሰዋል::
Image may contain: 5 people, people smiling, people sitting

Comments

Popular posts from this blog

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ

በዜሮ ዓመት የወጣ ክፍት የስራ ማስታወቂያ

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት