በመማሪያ ክፍል ጥበትና መምህራን እጥረት ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየተፈጠረ መሆኑን የጣፎ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገለፀ::

- በመማሪያ ክፍል ጥበትና መምህራን እጥረት ምክንያት የመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እየተፈጠረ መሆኑን የጣፎ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ገለፀ::

- የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰና የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም የምገባ ፕሮግራም ያልጀመሩ የአባዶና ጣፎ ትምህርት ቤቶችን ጎብኝተዋል::
--------------------------------------
Image may contain: 10 people, child
የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 4/2012 ዓ.ም)
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የጣፎ መጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የመማሪያ ክፍል ጥበት : የመምህራን እጥረት : የውሐና መብራት መቆራረጥ : የምግብ ማብሰያና መመገቢያ አዳራሽ : የአጥር እንዲሁም የግቢ ማስፋፊያ ችግር እንዳለበት አስታወቀ:: ትምህርት ቤቱ 4650 ተማሪዎችን መዝግቦ ትምህርት ቢጀምርም የተማሪ ቁጥር ከመማሪያ ክፍል ጋር አለመጣጣሙን ገልፇል:: በትምህርት ቤቱ የተማሪ ክፍል ጥምርታ ለኬጂ 1 ለ 105 : ለ1ኛ ደረጃ ደግሞ 1 ለ 70 መሆኑን ተመልክተናል::
Image may contain: 7 people, crowd and indoor
በትምህርት ቤቱ የተማሪዎች ምገባ ያልተጀመረበትን ምክንያት እንዲያብራራ ተጠይቆ የማብሰያ ችግር አለብኝ ብሏል:: ምገባውን ለማድረግ የተደራጁ ሴቶች ብድር እንዳልተመቻቸላቸውና በራሳቸው አቅም ምገባ ማስጀመር እንደማይችሉ ተናግረዋል::
የየካ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ለገሰ ጥያቄው ተደራጅቶ ለአስተዳደሩ እንዳልቀረበ ጠቅሰው የመሰረተ ልማት : የአጥርና ማስፋፊያ ጥያቄ በአጭር ጊዜ እንደሚፈታ ተናግረዋል:: ከክፍል ጥበት ጋር የተያያዘው ችግር ተጨማሪ ክፍሎች እስኪገነቡ መማር ማስተማሩን በፈረቃ በማድረግ ት/ቤቱ ሊፈታ እንደሚገባው አቅጣጫ ተቀምጧል::
Image may contain: 1 person, standing, sky and outdoor
በየካ ወረዳ 14 አባዶ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በበኩሉ የመምህር እጥረት : የኪችንና የመመገቢያ አዳራሽ ችግር እንዳለበት ተናግሮ ምገባውን ያልጀመርኩት ማብሰያ ቦታ ስለሌለኝ ነው ብሏል:: በዚህ ት/ቤት መዋዕለ ህፃናትን ጨምሮ 7900 ተማሪዎች የሚገኙ ሲሆን በአንዳንድ መማሪያ ክፍሎች መምህራን እንደሌሉ ተዘዋውረን አረጋግጠናል::
Image may contain: 9 people, people sitting, table and indoor
በከተማ አስተዳደሩ የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከትላንት ሰኞ ጀምሮ እንዲካሄድ አቅጣጫ ቢቀመጥም በክፍለ ከተማው ምገባ የጀመሩ ትምህርት ቤቶች 7 ብቻ ናቸው:: ይህ ችግር በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንደሚፈታ ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::

Comments

Popular posts from this blog

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ