በኢሬቻ ዙሪያ የህዝብ ውይይት ተደረገ::

*ብረተሰቡ የኢሬቻ በዓል እንግዶችን በፍቅር ተቀብሎ በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንዲሸኝ ጥሪ ቀረበ::

*ለመዲናችን አዲስ አበባ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል::
*በአሉን ለማክበር ከተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ከ10 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ወደመዲናዋ ይመጣል::
***************************************




በኢሬቻ በአል ምንነትና አከባበር ስነ ስርዓት ዙሪያ ከተለያዩ የህብረተሰቦች ክፍሎች ጋር በየካ ክፍለ ከተማ የፖናል ውይይት ተደርጏል:: ህብረተሰቡ የበዓሉን እንግዶች በፍቅር ተቀብሎ በፍፁም ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንዲሸኝ ጥሪ ቀርቧል::

ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ከክረምት ወራት ወደ ብርሐን ላሸጋገረው ዋቃ(አምላክ) ምስጋና የሚያቀርብበት : ህዝቡ አንድነቱን የሚያጠናክርበት : ባህሉንና ስርዓቱን የሚያስተዋውቅበት : የፖለቲካ የሀይማኖትና ሌላ አስተሳሰብ ሳይገድበው በጋራ የሚሰባሰብበት የገዳ ስርዓት አካል መሆኑ ተገልፇል::

በአሉ በአመት 2 ጊዜ በክረምት ወራት ማጠናቀቂያና በበጋ ወራት መጨረሻ በጋራ ይከበራል:: የመጀመሪያው ኢሬቻ ቢራ የተሰኘው በአል በወንዝ አካባቢ በክረምት ወራት መጨረሻ የፊታችን መስከረም 24 የሚከበር ሲሆን ኢሬቻ አርፋሳ ደግሞ በበጋው ማጠናቀቂያ ወቅት በተራራ አካባቢ ይከበራል ተብሏል::

በአዲስ አበባ በሚከበረው ኢሬቻ ከመላው ኦሮሚያ ከ10 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል:: በአሉ ለከተማዋ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑንና ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደሚያስገኝ ነው የተገለፀው::

Comments

Popular posts from this blog

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ