በህገወጥ መንገድ ባልተፈቀደ ቦታ ሲሸጥ የነበረ 183 ኩንታል ሲሚንቶ ተወረሰ።

በህገወጥ መንገድ ባልተፈቀደ ቦታ ሲሸጥ የነበረ 183 ኩንታል ሲሚንቶ ተወረሰ።=========================

No photo description available.

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 አስተዳደር በተለምዶ ሲሚንቶ ተራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ከተፈቀደላቸው ህጋዊ ቦታ ውጪ የእግረኛ መንገድ በመዝጋት ሲሚንቶ ሲሸጡ የነበሩ ነጋዴዎች ላይ በተወሰደ ኦፕሬሽን 183 ኩንታል ሲሚንቶ መውረሱን በክ/ከተማው ሰላምና ጸጥታ የደንብ ማስከበር ዘርፍ አስታውቋል።
የደንብ ማስከበር ዘርፍ አስተባባሪ ኮ/ል ግርማ ደመቀ እንዳሉት ነጋዴዎቹ የሚፈፅሙት ተግባር ህገወጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ቢሰጣቸውም ከድርጊታቸው ባለመቆጠባቸው ጥቅምት 7/2012 ዓ.ም የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ከወረዳው ባለድርሻ አካላት እና ከጸጥታ ሀይል ጋር በወሰደው እርምጃ 183 ኩንታል ሲሚንቶ መውረሱንና ለመንግስት ገቢ ማድረጉን ገልጸዋል ሲል የክፍለ ከተማው ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት በፌስቡክ ገጹ ዘግቧል።

Comments

Popular posts from this blog

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ

በዜሮ ዓመት የወጣ ክፍት የስራ ማስታወቂያ

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት