21ኛው የጤና ጉባኤ በእንጦጦ ቁጥር 2 ጤና ጣቢያ ተካሔደ::

21ኛው የጤና ጉባኤ በእንጦጦ ቁጥር 2 ጤና ጣቢያ ተካሔደ::

-----------------------------------
Image may contain: 14 people, people smiling, people standing and outdoor
የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 3/2012 ዓ.ም)
'ዘርፈ ብዙ ትብብር ለጤናማና የበለፀገች ሐገር' በሚል መሪ ቃል እየተካሔደ ያለውን ሀገር አቀፍ የጤና ጉባኤ ምክንያት በማድረግ በየካ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት በእንጦጦ ቁጥር 2 ጤና ጣቢያ በተለያዩ ፕሮግራሞች ተከብሯል::
በጉባኤው የቤተሰብ ጤና ክብካቤ አሀድ (PHC) ትግበራ ሪፖርት ከሁሉም ክልሎችና ከጤና ቢሮ ለተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል:: ከክልል የመጡ የልምድ ልውውጥ ልዑካን የቤተሰብ ጤና ክብካቤ አሀድ አተገባበር ሁኔታን ጎብኝተዋል:: ልዑካን በባለሙያ ፍልሰትና እጥረት : በፕሮግራሙ ቀጣይነት : በአንቡላንስ አገልግሎት ተደራሽነትና በማበረታቻ ስርዓት ዙሪያ ጥያቄ አንስተዋል::
Image may contain: 2 people, people smiling, suit
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በበኩሉ የቤተሰብ ጤና አሀድ ፕሮግራም ዘላቂ ስርዓት ሆኖ እንዲቀጥል እየሰራሁ ነው ብሏል:: በዚህ ፕሮግራም ትግበራ ወቅት ከባለሙያ ጋር የተያያዙ ችግሮችን በየጊዜው በመፍታት በአገልግሎቱ ተደራሽነት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሆነም ተብራርቷል::
ከ50 በላይ ከአፍሪካና ከሀገር ውስጥ የተውጣጡ የጤና ተቋማት ባለሙያዎች በጤና ጣቢያው ተገኝተው የቤተሰብ ጤና አሀድ ትግበራ ልምድ ወስደዋል::
እንጦጦ ቁጥር 2 ጤና ጣቢያ በ90 የጤና ባለሙያዎች ለ40,262 የህብረተሰብ ክፍሎች በ5 የቤተሰብ ጤና ቡድኖች የቤተሰብ ጤና አገልግሎትን ፕሮግራምን መተግበር ከጀመራ 4 አመታትን አስቆጥሯል::
Image may contain: 8 people, people sitting

Comments

Popular posts from this blog

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ