መሰረተ የካ ህብረት ስራ ዩኒየን 5 ሚልዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ገለፀ::

መሰረተ የካ ህብረት ስራ ዩኒየን 5 ሚልዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን ገለፀ::

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
(የካ ማህበራዊ ሚዲያ ጥቅምት 2/2012)
Image may contain: 2 people, indoor
መሰረተ የካ ህብረት ስራ ዮኒየን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል:: በጉባዬው የ2011 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2012 በጀት አመት እቅድን በተመለከተ ከህብረት ስራ ዮኒየን አመራሮች ጋር ገምግሟል::
በ2011 ከ59 ተቋማት ጋር ውል በመፈፀም 199 አይነት ምርቶችን ማቅረብ መቻሉን: በዓላትን ምክንያት በማድረግና 6ኛው ሀገር አቀፍ ባዛርና ኤግዝብሽን ማዘጋጀት መቻሉ: ከመሰረታዊ ማህበራት ጋር መድረኮችን በመፍጠር ግንኙነቱን ማጠናከር እና ውጤት ማስመዝገብ መቻሉ :የግብርና ምርቶች አቅርቦት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱና ለክረምት የሚሆን 5000 ኩንታል ጤፍ ክምችት መያዝ መጀመሩ: ለበዓላት ዶሮ: እንቁላል: ቅቤ: አይቤ እና የስጋ በሬ በማቅረብ ገብያ ማረጋጋት መቻሉን በሪፖቱ አቅርቧል::
በበጀት አመቱ የተገኙ የገቢና የወጪ አፈፃፀም ከኢንዱስትሪና ከግብርና ምርት ሽያጭ 146,342,236.02 ብር እና ከማዳበሪያና ከካርቶን ሽያጭ 20,613.00 ገቢ መገኘቱን በሌላ በኩል በቆጠራ 2,155,507.19 ብር : በግዥ 138,970,773.42 ብር: ጠቅላላ ለሽያጭ የቀረበ 141,126,280.61 ብር እና አስተዳደራዊ ወጪ 1,880,447.19 ብር ማውጣቱን በኦዲት ሪፖርት አቅርቧል::
ከጉባኤው ተሳታፊዎች ለበአል ተገዝተው የተሰራጩ የዶሮና በሬ ግዢ ግልፀኝነት : ከኦዲት ግኝት ሪፖርት እና ከቦርድ አመራርነት በራሳቸው ፍቃድ ስለለቀቁ አባል ጥያቄዎችን አንስተዋል::
ለተነሱ ጥያቄዎች የየካ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ መለሰ ጋሻው ዩኒየኑ ብዙ ውጣ ውረድ ማሳለፉን ገልፀው ከ10ሩም ክፍለ ከተሞች የመጨረሻ የነበረ የህብረት ስራ ማህበር 6ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከመላው ኢትዮጵያ 1ኛ የወጣው እናንተ በሰራችሁት ስራ ስለሆነ መኩራት አለባችሁ ብለዋል::
Image may contain: 2 people, people sitting and indoor
አቶ መለሰ ከኦዲትና ከአመራር መልቀቅ ጋር ለተያያዙ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል::
በ2012 በጀት አመት የግብርና ምርት ክምችት አምና ከነበረው 5000 ኩንታል ወደ 15000 ኩንታ ማሳደግ: የኢንዱስትሪ ምርት አምና ከነበረው ግብይት ማሳደግ: ዩኒየኑን በሰው ሀይል ማሟላትና በመዋቅር ማጠናከር: ለግብርናና ለኢንዱስትሪ ምርት ማጏጏዣ የሚሆን የመኪና ግዥ መፈፀም እና የመሳሰሉ ዋና ዋና ስራዎችን ለመስራት በእቅድ ተይዧል::

Comments

Popular posts from this blog

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ