ጌጅ ኮሌጅ ለህዝባዊ ሰራዊት አፀደ ህፃናት ት/ቤት የወንበርና ጠረጴዛ ድጋፍ አደረገ::

ጌጅ ኮሌጅ ለህዝባዊ ሰራዊት አፀደ ህፃናት ት/ቤት የወንበርና ጠረጴዛ ድጋፍ አደረገ::

-------------------------------------------
Image may contain: 2 people, people standing, suit and outdoor
የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 5/2012 ዓ.ም)
ጌጅ ኮሌጅ ለህዝባዊ ሰራዊት አፀደ ህፃናት ትምህርት ቤት 100 መቀመጫ ወንበርና 25 ጠረጴዛ ድጋፍ አደረገ:: የኮሌጁ ፕሬዝዳንት አቶ ሞገስ ሲሳይ መንግስት በትምህርት ስራ ላይ እያደረገ ያለውን በጎ ተግባር የማገዝ ግዴታ ስላለብን ድጋፉን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል:: ኮሌጁ ከዚህ በፊት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ አይዘነጋም:: ለችግረኞችና ለመንግስት ሰራተኞች በዝቅተኛ ክፍያና በነፃ የትምህርት እድል ድጋፍ በማድረግ በትምህርት ዘርፍ ሀላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነም ተነግሯል::
Image may contain: 5 people, people smiling, people standing and outdoor
የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብዮት ድንቁ በ2012 በጀት አመት ለትምህርት ስራው የመንግስትን ስራ በማገዝ ባለሀብቶች ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረጉ መሆኑን ገልፀው ኮሌጁ ላደረገው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል::
የትምህርት ቤቶችን የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለመፍታት የክፍለ ከተማው ወተመህ ተወካዮች ባለሀብቶችን በማስተባበር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ::
No photo description available.

Comments

Popular posts from this blog

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ