የየካ ክፍለ ከተማ ባህል :ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ፅ/ቤት የአለም የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ የእውቅ እና ሽልማት በማዘጋጀት የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ::

የየካ ክፍለ ከተማ ባህል :ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ፅ/ቤት የአለም የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ የእውቅ እና ሽልማት በማዘጋጀት የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ::
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 6/2012)
Image may contain: 3 people, people smiling, people standing
የክፍለ ከተማው ባህል :ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ፅ/ቤት በአለም አቀፍ ደረጃ ለ 40ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ32 ጊዜ ሲከበር የቆየው የቱሪዝም ሳምንትን አስመልክቶ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የማጠቃለያ ፕሮግራም አካሄደ::
በፕሮግራሙ በአዲስ አበባ ከተማ ባህል :ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የተዘጋጀ የቱሪዝም ጥናታዊ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በሰንዱ የቱሪዝም ትርጏሜ: የቱሪዝም አይነቶች: የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ዋና ዋና አካላት: ከዘርፍ የተገኙ ጠቀሜታዎችና በከተማው ቱሪዝም ዘርፍ ያሉ ተግዳሮቶች ተዳሰዋል::
የቀረበውን ሰነድ መሰረት በማድረግ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች በአዲ አበባ ከተማ ያልተጎበኙ በረካታ ቅርሶች መኖራቸውን በመጥቀስ በተቀናጀ መልኩ መጎብኘት እንደሚገባ አስተያየት ሰጥተዋል::
የቱሪዝም ቀንን ችግኝ በመንከባከብ: ጉብኝት በማድረግ እና ሲፖዝየም በማዘጋጀት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ 3 ወረዳዎች የእውቅና ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን በክረምት መረሀ- ግብር የኪነ-ጥበብ ስልጠና ለወሰዱ ግለሰቦችና ስልጠናውን ለሰጡ አካላት በክፍለ ከተማው አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ በአቶ አለሙ ኢብሮ አማካኝነት የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል::
Image may contain: 7 people, people sitting

Comments

Popular posts from this blog

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ