በኢሬቻ የማንኛውም ፓርቲ ባንዲራ መያዘ ተከለከለ::
- በኢሬቻ በዓል የማንኛውም ፓርቲ ባንዲራና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ፅሁፎችን ያዘሉ ቲሸርቶችና ህትመቶች ይዞ መግባት እንደማይቻል ተገለፀ::
- የኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፀጥታ ሀይሎችና ከህዝብ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት ተደርጏል::
______________________________________________
(መስከረም 21/2012)
የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የኢሬቻ በአል በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፖሊሶችና የህዝብ አደረጃጀቶች ጋር ውይይት አድርጏል:: ከበዓሉ አርማ ውጪ የማንኛውም ፓርቲ ባንዲራ ይዞ መሳተፍ እንደማይቻልና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ የህትመት ውጤቶችን መጠቀም ክልክል መሆኑን ፖሊስ አስታውቋል:: በዓሉን ለፖለቲካ ፍጆታ ለመጠቀና የበዓሉን ገፅታ ለማጠልሸት በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራ መሆኑን አስተዳደሩ ገምግሟል:: ህብረተሰቡና የበዓሉ ተሳታፊም የነዚህ ርካሽ ፖለቲከኞች አላማ እንዳይሳካ እንዲያደርግና ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል::
በክፍለ ከተማው ከ50 ሽህ በላይ ህዝብ በዓሉ በሰላም በሚጠናቀቅበት ሁኔታ ምክክር መደረጉንና የበዓሉን ሰላም ለማረጋገጥ ለ1500 በበጎ ፈቃደኝነት ፍተሻ የሚያደርጉ ፎሌዎች ስምሪት መስጠቱን አስተዳደሩ ገልፇል::
ክፍለ ከተማው እንግዶች ከሚገቡባቸው በሮች አንዱ እንደመሆኑ ጥብቅ ፍተሻና ክትትል እንደሚደረግና በበዓሉ ዕለት ከላምበረት መነኻሪ ጀምሮ ወደመኻል ከተማ የትራፊክ እንቅስቃሴ አይኖርም ተብሏል::
Comments
Post a Comment