ለስደት ተጋላጭ ለሆኑ 47 ወጣቶች የስራ ፈጠራ ስልጠና መስጠቱን የየካ ክፍለ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ገለፀ::

ለስደት ተጋላጭ ለሆኑ 47 ወጣቶች የስራ ፈጠራ ስልጠና መስጠቱን የየካ ክፍለ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ገለፀ::---------------------------------------



የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 6/2012 ዓ.ም)
Image may contain: 10 people, people sitting
የየካ ክፍለ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ፕላን ኢንተርናሽናል ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ለስደት ተጋላጭ ለሆኑ 47 ወጣቶች ለ7 ተከታታይ ቀናት በስራ ፈጠራ ዙሪያ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ገልፇል::
እንደ ፅ/ቤቱ ገለፃ ወጣቶቹ የስራ እቅድ አውጥተው እና ተደራጅተው ወደስራ የሚገቡ ሲሆን በሰሩት እቅድ መሰረት ፕላን ኢንተርናሽናል የመነሻ ካፒታል ነፃ ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ተነግሯል::
ሰልጣኞቹ በበኩላቸው የወሰዱት ስልጠና በህይወታቸው : በስራ ሰአት አጠቃቀማቸው : ችግሮችን እንዴት መሻገር እንደሚቻልና በንግድ ስራቸው ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል መሆኑን ገልፀው ህጋዊ ሰውነት ለማግኘት በሚያደርጉት እንቅስቃሴና በመስሪያ ቦታ በኩል ችግር ሊገጥማቸው እንደሚችል ተናግረዋል::
የፅ/ቤቱ ሀላፊ ወ/ሮ ማያ ታደሰ ወጣቶቹ ስራ ፈላጊ መሆናቸው ተረጋግጦ የተመለመሉት በስራ ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ፅ/ቤት በኩል እንደሆነና በፍጥነት ወደስራ እንዲገቡ ከአዲስ ካፒታልና ሌሎች ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል::
ወጣቶቹ ህጋዊ እውቅና ካገኙ በሗላ በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ወደስራ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል::
Image may contain: 6 people, people sitting and indoor

Comments

Popular posts from this blog

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ