የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት አስታወቀ::

እድሜያቸው 14 አመት ላልሞላቸው በሁሉም የመንግስትና የግል ት/ቤት ለሚማሩ ልጃ ገረዶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ሊሰጥ መሆኑን የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት አስታወቀ::---------------------------------------------

የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ጥቅምት 6/2012 ዓ.ም)
No photo description available.
የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት ከጥቅምት 10-14/2012 ድረስ እድሚያቸው 14 አመት ከ9-14 ለሆኑ ልጃ ገረዶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ በላከው ደብዳቤ አስታውቋል:: ክትባቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ እንደሚሰጥ የገለፀው ፅ/ቤቱ በሁሉም 1ኛና 2ኛ ደረጃ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የክትባት ዘመቻው ይካሄዳል ብሏል::
የክፍለ ከተማው ነዋሪም ሆነ የትምህርት ማህበረሰብ በዚህ ክትባት ሁሉም ልጃ ገረዶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ እንዲያደርግ ፅ/ቤቱ ጥሪውን አስተላልፏል::

በዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ ጥናት መሰረት በኢትዮጵያ የካንሰር በሽታ ገዳይነት ምጣኔ 4 በመቶ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን በማህፀን ካንሰር ቫይረስ 24 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶች ተጋላጭ ናቸው:: በኢትዮጵያ በየዓመቱ 7000 ያህል ሴቶች በማህፀን በር ካንሰር ሲያዙ ከእነዚህ ውስጥ 5000 ያህሉ እንደሚሞቱ ጥናቱ ያመለክታል::
የማህፀን በር ካንሰር መንስኤው human papilloma virus/HPV/ የሚባል በግብረ ስጋ ግንኙነት በቀላሉ የሚተላለፍ ቫይረስ ሲሆን ሁለቱንም ፆታዎች እንደሚያጠቃና በወንዶች የመራቢያ አካል ኪንታሮት (genital wart) የሚባለውን በሽታ ሲያመጣ ሴቶች ላይ ግን የማህፀን በር ካንሰርን ያስከትላል::

Comments

Popular posts from this blog

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

አዋጅ ቁጥር 1064/2010

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ