Posts

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት

Image
አዲሱ የነጥብ ስራ ምዘና ደረጃ የወጣላቸው የስራ መደቦች ================================= የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጠናው የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት መሰረት በከተማ አስተዳደሩ በመሰረታዊ የስራ ሂደት ጥናት ለተፈጠሩ ስራ መደቦች የኮንቨርሽን ስራ በማከናወን በክፍለ ከተማ እና በወረዳ ደረጃ የስራ መደብ ስታንዳርድና ደረጃ የ32 ፅ/ቤቶችን ስራ መደቦች ልኮልናል:: በዚህ መሰረት በዋና ስራ አስፈፃሚ ስር ለሚገኙ መደቦች የተደረገውን የመደብ ኮንቨርሽን እነሆ:: ኤክሲኪዩቲብ ሴክሬታሪ 2 - ፅሂ-11 ወደ ኤክሲኪዩቲቭ ሴክሬታሪ 1 (ደረጃ 9) - ፅሂ-10 ወደ ሴክሬታሪ 2 ደረጃ 8 - ፅሂ-9 ወደ ሴክሬታሪ 2 ደረጃ 8 - ፅሂ-8 ወደ ሴክሬታሪ 1 (ደረጃ 😎 - እጥ-7 ሾፌር ወደ ሹፌር 1 (ደረጃ 6) - የህግ አገልግሎት አማካሪ ፕሳ-7 ወደ የህግ ባለሙያ 4 (ደረጃ 14) - የስነ ምግባር መኮንን ፕሳ-6 ወደ ስነ ምግባር መኮንን 3 (ደረጃ 11) - የእቅድ ዝግጅትና ግምገማ ባለሙያ ፕሳ-6 ወደ ደረጃ 10 - የህዝብ ግንኙነት ከፍተኛ ባለሙያ ፕሳ 7 ወደ ህዝብ ግንኙነት ባለሙያ 4 ደረጃ 13 - የህዝብ ግንኙነት መካከለኛ ባለሙያ ፕሳ-6 ወደ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ 3 ደረጃ 10 - የቪዲዮ ካሜራ ማን መፕ 8 ወደ ካሜራ ማን 2 ደረጃ 7 - የፎቶ ካሜራ ማን መፕ 7 ወደ ካሜራ ማን 1 ደረጃ 6 - የህትመት ውጤቶች ዋና አዘጋጅ ፕሳ-7 ወደ ደረጃ 12 - የድረገፅ አማርኛ ቋንቋ ሪፖርተር ፕሳ 4 ወደ ደረጃ 10 - የድረገፅ እንግሊዝኛ ቋንቋ ሪፖርተር ፕሳ 4 ወደ ደረጃ 10 - የዳታ ቤዝ አስተዳደር ባለሙያ ፕሳ...

ክፍት የስራ ማስታወቂያዎች

Image
ክፍት የስራ ማስታወቂያዎች -------------------------------- በ0 ዓመትና ልምድ ለሚጠይቁ 82 መደቦች #share በማድረግ ስራ ለሚፈልጉ ሁሉ አድርሱ 1. የኢትዮጵያ ወጣቶች አካዳሚ በ0 ዓመት ጀማሪ ቮሊቦል አሰልጣኝ 2 : ጀማሪ ብስክሌት አሰልጣኝ 2 : ጀማሪ ውሀ ዋና አሰልጣኝ 2 : ጀማሪ የቦክስ አሰልጣኝ : የቦክስ ረዳት አሰልጣኝ : ጀማሪ የጠረጴዛ ቴንስ አሰልጣኝ : ረዳት የጠረጴዛ ቴንስ አሰልጣኝ : የሪከርድና ማህደር ሰራተኛ : ሞተረኛ : የጉልበት ሰራተኛ እና አትክልተኛ በድምሩ 19 ሰራተኞችን መቅጠር ይፈልጋል:: ልምድ የሚጠይቁ መደቦችም አሉት : ከ12/03/2012 ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ዋና መስሪያ ቤት ገርጂ የቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ቢሮ ቁጥር 107 ቀርባችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብላችሗል:: 2. ትራንስፖርት ሚኒስቴር ልምድ ለሚጠይቁ 33 መደቦች ብቁ ባለሙያ መቅጠር ይፈልጋል:: ከዛሬ ጀምሮ በ7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ብሔራዊ ፖስታ ቤት አካባቢ በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት እንድትመዘገቡ ጋብዟችሗል:: 3. የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ በ0 ዓመት የሰው ሀብት አስተዳደር ባለሙያ : የሪከርድና ማህደር ባለሙያ እንዲሁም ተላላኪ በድምሩ 6 ባለሙያዎችን በልምድ 1 1 የሰው ሀብት አስተዳደር ባለሙያ ይፈልጋል:: አድራሻቸው መገናኛ አምቼ ኩባንያ ዝቅ ብሎ ይገኛል:: 4. አለርት ሆስፒታል ሜዲካል ስፔሻሊስ/ ኢመርጀንሲ ሜድስን ኤንድ ክሪቲካል ኬር/ ይፈልጋል:: ከዛሬ ጀምሮ አየር ጤና ሳይደርስ የቀድሞው ዘነበወርቅ ሆስፒታል መጥታችሁ ተመዝገቡ ብሏችሗል:: ለበለጠ መረጃ አዲስ ዘመን ጋዜጣ የሕዳር 12 እና 13/2012 ዓ.ም እትሞ...

የብልፅግና ፓርቲ  (ብልፅግና)  መተዳደሪያ ደንብ (ረቂቅ)  

የብልፅግና ፓርቲ (ብልፅግና)  መተዳደሪያ ደንብ  መግቢያ   በኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) እና በአጋር ድርጅቶች አመራር በአገራችን ያስመዘገብናቸውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ለውጦችን አስጠብቆ ለማስፋት፣ ስህተቶችን ለማረም እና የመጪውን ትውልድ ጥቅምና ፍላጎት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የድርጅታችንን ቅርጽና ይዘት ወቅቱ ለሚጠይቀው ትግል በሚመጥን መልኩ መቀየር በማስፈለጉ፤  የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችና አጋር ድርጅቶች ሀገር በመራንባቸው ዓመታት በአመዛኙ ተመሳሳይ የፖለቲካ ዓላማ፣ ፕሮግራም እና መሰረታዊ አቅጣጫ እየገነባን የመጣን በመሆኑ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል እና ስህተቶችን በማረም ወደ ሚቀጥለው የትግል ምዕራፍ ለመሸጋገር አስቻይ አቅም ያለን በመሆኑ፤ የምናካሂደው ውህደት እያንዳንዱ ድርጅት የነበረውን የአላማና የተግባር ውህደት በአዲስ መንፈስ ይበልጥ በማጠናከር የተሻለ ኃይል እንድናሰባስብ የሚያስችለን በመሆኑ፤  በኢሕአዴግ ድርጅታዊ ጉባዔዎች የፓርቲ ውህደት አጀንዳ በተከታታይ ቢነሳም ሳይወሰንና ሳይፈፀም መቆየቱን ግምት ውስጥ በማስገባት 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ የዝግጅት ስራዎች በፍጥነት ተጠናቀው ድርጅቶቹ ወደ ውህደት እንዲሸጋገሩ ያስቀመጠውን አቅጣጫ መፈፀም በማስፈለጉ፤  ሀገራችን ኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች እና የተለያዩ ማንነቶች በጋራ ባካበቱት እሴት የተገነባችና የጋራ ራዕይ ያላቸው ህዝቦች መኖሪያ ህብረ ብሄራዊት ሀገር መሆኗን በመገንዘብ፣  የሃገራችን ኢትዮጵያን እድገትና የጋራ ብልፅግና እውን ለማድረግ ጠንካራና ቅቡልነት ያለው ሀገረ መንግስት መገንባት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ፣ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረ...

“ንፁህ እጆችና መፀዳጃ ቤት ለሁሉም”

Image
ዓለም አቀፍ እጅ የመታጠብና መፀዳጃ ቤት ቀን “ንፁህ እጆችና መፀዳጃ ቤት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል በየካ ክፍለ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡ የካ ማህበራዊ ሚዲያ (ሕዳር 10/2012 ዓ.ም) የየካ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት ዓለም አቀፍ እጅ የመታጠብና መፀዳጃ ቤት ቀንን በትምህርት ቤቶች ተገቢንት ያለው የእጅ አስተጣጠብ ስርዓትን በማስተማር እየተከበረ ይገኛል፡፡  የዘንድሮው የእጅ መታጠብ ቀን “ንፁህ እጆችና መፀዳጃ ቤት ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ ይውላል፡፡ ለመሆኑ እጅ መታጠብ ለምን ያስፈልጋል? እጅ የመታጠቢያ ወሳኝ ጊዜያት የትኞቹ ናቸው? እጃችን ስንታጠብስ ትኩረታችን ምን ላይ ይሁን? በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ ይዘንላችሁ ቀርበናል ተከታተሉን፡፡  የማህበራዊ ሚዲያ መከታተያ ቻናሎቻችን ከፌስቡክ በተጨማሪ፡ yekasec.blogspot.com ·          www.youtube.com/yekatube/  መመልከት ትችላላችሁ! 1.        እጅ መታጠብ ለምን ያስፈልጋል ----------------------------- የተለያ ተግባራትን በምንሰራበት ወቅት እጃችን የተለያዩ ቆሻሻዎችንና በሽታ አምጪ ተሕዋስያንን ሊነካ ይችላል፡፡ እነዚህ ተህዋስያን ጥቃቅን በሆኑ የእጆቻችን መተጣጠፊያ ቦታዎች መደበቅና መራባት ስለሚችሉ ለተለያዩ በሽታዎች ይዳርጉናል፡፡ በትክክል እጅን መታጠብ ማለት የጤና ጠንቅ ከሆኑ ተህዋስያን ጋር የሚደረግ የ20 ሰከንድ ትግል ማለት ነው፡፡ ይህ ተግባር ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ሰዎች በቀላሉና በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚተገብሩት ፍቱን መድሐኒት ነው...

የ2012 በጀት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም

Image
በሩብ ዓመቱ በየካ ክፍለ ከተማ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ------------------------------------------------ 1. አዲሱን መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ተግባራዊ ከማድረግና ባለሙያ ከማብቃት አኳያ  በክፍለ ከተማ ደረጅ በተዋቀሩ አራቱም ፑሎች በተጠናው አዲሱ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ 1508 ሰራተኞችን ለመደልደል ታቅዶ  1150  ባላቸው ተፈላጊ ችሎታ ተመድበዋል፡፡ በ14ቱም ወረዳዎች በተጠናው አዲሱ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ 4324 ሰራተኞችን ለመደልደል ታቅዶ  4041 ባላቸው ተፈላጊ ችሎታ ተመድበዋል፡፡ በአራት ዙር ለ2845 በፐርሰናል ሊደር ሽፕ፤ ኢንፕሎይመንት ኢንጌጅመንትና ሰርቫንት ሊደር ሽፕ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ 2. ከመሬት ልማትና ማኔጅመንት ሥራችን አኳያ  አዲስ በሊዝ ለሚፈቀዱትና በምትክ ለሚሰጡ ለ30 ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ አዘጋጅቶ ለመስጠት ታቅዶ ለ18 አገልግሎት ፈላጊዎች አገልግሎቱን መስጠት ተችሏል፡፡ ከ1988 ዓ.ም እስከ 1997 ዓ.ም አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ ለተያዙ ይዞታዎች ካርታ የታተመ  6,833፤ ፕላን ተቃርኖ ሆኖ የተለየ 3880፤ በ1997 መስመር ካርታ ላይ የማይታይ 3463 መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ የሽማቾት የህብረት ስራ ማህበራት እስካሁን ድረስ 69 ይዞታዎች ካርታ እንዲሰራላቸዉ  የተጠይቀ ሲሆን  46  ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተዘጋጅቷል፡፡ ቀሪዎቹ 23 ይዞታዎች በተለያዩ ምክንያቶች ያልተሰራላቸዉ ሲሆን ሲተነተን፤ የጂ አይ ኤስ ወይም 1997 የመስመር ካርታ ላይ የማይታዩ በመሆናቸዉ የማይሰሩ 15 ፤ ኦቨር ላፕ 1፤ 7 በሂደት ላይ ያሉ ናቸው፡፡ ለ3...