የ2012 በጀት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም

በሩብ ዓመቱ በየካ ክፍለ ከተማ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

------------------------------------------------


1. አዲሱን መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ተግባራዊ ከማድረግና ባለሙያ ከማብቃት አኳያ 


  • በክፍለ ከተማ ደረጅ በተዋቀሩ አራቱም ፑሎች በተጠናው አዲሱ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ 1508 ሰራተኞችን ለመደልደል ታቅዶ  1150  ባላቸው ተፈላጊ ችሎታ ተመድበዋል፡፡
  • በ14ቱም ወረዳዎች በተጠናው አዲሱ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ 4324 ሰራተኞችን ለመደልደል ታቅዶ  4041 ባላቸው ተፈላጊ ችሎታ ተመድበዋል፡፡
  • በአራት ዙር ለ2845 በፐርሰናል ሊደር ሽፕ፤ ኢንፕሎይመንት ኢንጌጅመንትና ሰርቫንት ሊደር ሽፕ ለባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

2. ከመሬት ልማትና ማኔጅመንት ሥራችን አኳያ 


  • አዲስ በሊዝ ለሚፈቀዱትና በምትክ ለሚሰጡ ለ30 ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ አዘጋጅቶ ለመስጠት ታቅዶ ለ18 አገልግሎት ፈላጊዎች አገልግሎቱን መስጠት ተችሏል፡፡
  • ከ1988 ዓ.ም እስከ 1997 ዓ.ም አግባብ ባለው አካል ሳይፈቀድ ለተያዙ ይዞታዎች ካርታ የታተመ  6,833፤ ፕላን ተቃርኖ ሆኖ የተለየ 3880፤ በ1997 መስመር ካርታ ላይ የማይታይ 3463 መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
  • የሽማቾት የህብረት ስራ ማህበራት እስካሁን ድረስ 69 ይዞታዎች ካርታ እንዲሰራላቸዉ  የተጠይቀ ሲሆን  46  ይዞታዎች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ተዘጋጅቷል፡፡ ቀሪዎቹ 23 ይዞታዎች በተለያዩ ምክንያቶች ያልተሰራላቸዉ ሲሆን ሲተነተን፤ የጂ አይ ኤስ ወይም 1997 የመስመር ካርታ ላይ የማይታዩ በመሆናቸዉ የማይሰሩ 15 ፤ ኦቨር ላፕ 1፤ 7 በሂደት ላይ ያሉ ናቸው፡፡
  • ለ3158 የመንግስት ቤቶች (የቀበሌ ቤት)  ካርታ ህትመት ተሰርቷል፡፡
  • ካሳ የተሰጣቸው የልማት ተነሺዎች ብዛት በቁጥር 50 ታቅዶ 21 ተከናውኗል፡፡

3. ከሥራ ዕድል ፈጠራ ስራችን፡- 


  • በመደበኛ፣ በመንግስት ፕሮጀክቶችና ተቋማት እና በግል ድርጅቶች፡- የተለየ ትኩረት በመስጠት እና ርብርብ በማድረግ በድምሩ ለ4507 ስራ ለመፍጠር ታቅዶ 4810 ተከናውኗል፡፡ 3374 ቋሚና ጊዚያዊ 1436 የስራ እድል ተፈጥሯል፡፡
  • በሩብ  አመት  7200 ስራ ፈላጊ ዜጎችን በ 1051 ኢንተርፕራይዞች በማደራጀት የሥራ ዕድልን ለመፍጠር ታቅዶ ለ2534 አንቀሳቃሾችን ያቀፉ 598 ኢንተርፕራይዞችን ማደራጀት ተችሏል፡፡ ከዚህ ውስጥ 28 በመቶ ሴቶች እና 90 በመቶ ወጣቶች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

4. ከምግብ ዋስትናና ልማታዊ ሴፍቲኔት ስራችን አንጻር ፡- 


  • የከተማ ውበትና አረንጓዴነት ልማት ስራችን ለ13,024 ተጠቃሚዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ13,024 የተቃሚዎች የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡-
  • በከተማ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ሥራ ለ3,778 ተጠቃሚዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ 3,778 የተቃሚዎችን የተደራጁ ሲሆን የተፋሰስ ሥራ እስከሚጀምር አያያዝና አወጋገድ ላይ በመስራት ይገኛሉ፡፡
  • በከተማ ግብርና ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ለ2,468 ተጠቃሚዎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ለ2,220 ተጠቃሚዎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡

5. የትምህርት ዘርፍ ተግባራት፡-

  • የቅድመ መደበኛ ትምህርት ሽፋን በማስፋት የቅበላ አቅም በ2011ዓ.ም 29241 የነበረውን ፤ ጥቅል ቅበላ ወደ 30569 ለማድረስ ታቅዶ 21573 (70 %)ማድረስ ተችለዋል::
  •  በተለያየ ምክንያት የትምህርት እድል ያለገኙ በየቀጠናው በተደረገ የቤት ለቤት  ቆጠራና ምዝገባ  እድሜያቸው ከ4-6 ዓመት የሆኑ ብዛት ወንድ 560 ሴት 420 አጠቃለይ 980 ቆጠራና ምዝገባ ማድረግ ተችሏል፡፡
  • ለጎልማሶች ትምህርት የትምህርት እድል ያላገኙ  ጎልማሶች ብዛት ወንድ 304  ሴት 1443 አጠቃላይ 1747 ተለይተዋል፡፡
  • የመምህራን ዝውውር ከክ/ከተማ ክ/ከተማ 110 መምህራን በዝውውር  መጥተው በየትምህርት ቤቱ ተመድበዋል፡፡
  • የውስጥ ዝውውር 45 መምህራን የተዘዋወሩ ሲሆን 25 መምህራን ተሸጋሽገዋል ፡፡ ከክልል በዝውውር  92 መምህራን በአፋን ኦሮሞና በሌሎች ት/ቤት ምደባ ተሰጥተዋል፡፡ ትምህርታቸውን ያሻሻሉ 2 በዲፕሎማ 5 በዲግሪ 6 በ2ኛ ዲግሪ መምህራን፣ ተሰጥቷል፡፡
  • 2115 የተማሪ ኮምባይልድ ዴስኮች እንድሁም ለአጸደ ህጻናት 1200 ወንበርና 400 ጠረጴዛ ከትምህርት መሳሪያዎች መምረቻና ማከፈፈያ ድርጅት ካቢኔ በማስወሰን ግዢ በመፈጸም ከተማሪ ቁጥር ጭማሪ ጋር በተያያዘ ለ22 ት/ቤቶች በማሰራጨት ችግራቸውን መቅረፍ ተችለዋል፡፡
  • 1,318,920 ደብተር፤  213,661 እስክሪብቶ ፣  103,194 እርሳስ  ተሰብስቦ በየት/ቤቶች ተሰራጭቷል፡፡ 
  • 27 ቅ/መደበኛ   ፤ 27 የመ/ደረጃ  እና  10 ሁለተኛ ደረጃ በድምሩ  ለ64 ት/ቤቶች እድሳት ተደርጓል፡፡

6  . በጤናዉ ዘርፍ፡-


  • ü  አጠቃላይ 6045 የዱቤ ህክምና ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
  • ü  284 በቫይረሱ ምክንያት ወላጆቻቸውን ላጡ እና ተጋላጭ ሕፃናት  ድጋና ክብካቤ ተደርጓል፡፡
  • ü   210 ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝባቸው ወገኖች ድጋፍና ክብካቤ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
  • ü  በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ከአዲስ እና ነባር ወረዳዎች 815,150.00 ገንዘብ ተሰብስቧል፡፡
  • ü  146 እናቶች የማህጸን ጫፍ ካንሰር ምርመራ እና ህክምና አግኝተዋል፡፡
  • ü  16718 ሰዎች የኤች.አይ. ምክርና ምርመራ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡ ከተመረመሩትና ኤች.አይቪ በደማቸው ውስጥ ከተገኘባቸው 336 ሰዎች ውስጥ 305 ህክምና ክትትል እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡

7.      ከምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ዘርፍ አንጻር፤-

ü  6 አዲስ ጤና ተቋም የሙያ ብቃት ፈቃድ 103 የጤና ተቋማት እድሳት 8 አዲስ የመድኃኒት ችርቻሮ ንግድ ፈቃድ ተሰጥቷል፡፡
ü  140 ኢንስፔክሽን በማድረግ አዲስ የብቃት ማረጋገጫ የምግብና መጠጥ ድርጅቶች ለመስጠት ታቅዶ 112 መስጠት ተችሏል፤
ü  73 ጤና ነክ ድርጅቶች አዲስ የብቃት ማረጋገጫ ለመስጠት ታቅዶ 49 መስጠት ተችሏል፤
ü  185 ጤና ነክ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ እንዲያድሱ ታቅዶ 121 ማደስ ተችሏል፡፡
ü  41,780 ብር የሚገመት 810 . ደህንነታቸውና ጥራታቸውን ያልጠበቁ ምግቦች ተወግደዋል፤
ü  29,215 ብር የሚገመት 1269 ሊትር ደህንነታቸውና ጥራታቸው ያልጠበቁ መጠጦች ተወግደዋል ፡፡
ü  2,020 ብር የሚገመት 64 ጥራታቸው ያልጠበቁ የተለያዩ የምግብ ማብሰያ ቁሳቁስ እንዲወገዱ ተደርጓል፡፡

8.       በኮንስትራክሽን ዘርፍ -

  • ü  በዚህ ሩብ 2011 . ወደ 2012 . የተሸጋገሩ ነባር ግንባታዎች ብዛት 34 ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ 11 90% እስከ 100% 9 ግንባታዎች 70% እስከ 90% 3 ግንባታዎች 50% እስከ 70% 6 ግንባታዎች 25% - 50% አፈፃፀም ደረጃ ላይ እንዲሁም 7 ግንባታ 25% በታች አፈጻጸም ላይ ይገኛሉ፡፡
  • ü   2012 . በእቅድ ከተያዙት ግንባታዎች ቅድመሁኔታቸው ተጠናቀው ወደ ግንባታ ከተገቡ 105 ግንባታዎች ውስጥ 101 ግንባታዎች 100% ተጠናቀዋል ፤  4 ግንባታዎች 95% እስከ 99% የሚገኙ  ናቸው፡፡
  • ü  በዘርፉ ለጥቃቅንና አነስተኛ 107 ማህበራት 150 ሚሊዩን ብር በላይ የገበያ ትስስር ተፈጥሯል ፡፡
  • ü  በመንግስት ግንባታዎች 967 ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡

9.      በቤቶች አስተዳደር ዘርፍ፡-

  • ü   ለችግረኛ የተሰጠ ቤት ብዛት 37  ለተሿሚዎች 3 በጠቅላላ 40 ቤቶች ተላልፈዋል፡:
  • ü  በበጎ ፍቃደኞች 196 ቤቶች እድሳታቸውን ማጠናቀቅ ተችሏል፡፡
  • ü   የወረዳ መኖርያ ቤት ውል እድሳት 4750   ታቅዶ 7094 ተከናውኗል 
  • ü   የቀበሌ ንግድ ቤት ውል እድሳት 972 ታቅዶ  1263 ማከናወን ተችሏል፡፡
  • ü   ከወረዳ ቤት ኪራይ ገቢ 695,106.00 ታቅዶ ክንውን 623983.64 ሲሆን ማከናወን ተችሏል፡፡ 
  • ü  ከወረዳ ንግድ ቤት ገቢ 2569502 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 2569502 ተሰብስቧል፡፡
  • ü  14428 ካርታ እንዲዘጋጅላቸው ለመሬት ልማትና ማኔጅመንት አስትዳደር ተላልፎ  የታተመ ካርታ ብዛት በፋይል 10533 በፓርሴል ብዛት 2962

10.      ከሰላምና ከጸጥታ ተግባራት አንጻር፡-


  • ü  በፍትሐ ብሔር ክትትል የተደረገባቸው 486 መዝገቦች ናቸው፡፡ ከነዚህ መዝገቦች  ውሣኔ ያገኙት በፍትሐ ብሔር 256 ናቸው፡፡ ውሣኔ ካገኙ መዝገቦች 224 ያህሉ ለመንግስት የተወሰኑ ሲሆን በመንግስት ላይ የተወሰኑ 32  መዝገቦች ናቸው፡፡
  • ü  በፍትሐ ብሔር የተከበረ የመንግስት ጥቅም ብር 1,425,646.73 / አንድ ሚሊየን አራት መቶ ሃያ አምስት ሺህ ስድስት መቶ አርባ ስድስት ብር ከሳባ ሦስት ሳንቲም/
  • ü  በፍትሐ ብሔር መንግስት ያጣው ጥቅም ብር 593,413.00 / አምስት መቶ ዘጠና ሦስት ሺህ አራት መቶ አስራ ሦስት ብር/ ነው፡፡
  • ü  በመንግስት ላይ የተወሰኑ መካከል ከቤት ይመለስልኝ ፤ ከካርታ አሰጣጥ ጋር የተያያዘ ከቀበሌ ቤት የመከራየት መብት ጋር በተያያዘ፤ ከውል ጋርና ከሰራተኛ ክርክር ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ናቸው፡፡  
  • ü  637  የመሬት ወረራዎች ተለይተው እርምጃ የተወሰደበት 604  33 እርምጃ አልተወሰደባቸውም፡፡
  • ü  151 ህገወጥ ግንባታ የፈፀሙ ግለሰቦች ተለይተው 115 ላይ እርምጃ ተወስዷል፡፡
  • ü  181 ህገ ወጥ ንግድ ላይ እርምጃ ተዋስዷል ፡፡
  • ü  ከቅጣት የተሰበሰበ ገቢ  461 795.00 ብር
  • ü  ለነዋሪዎች የመታወቂያ እና የነዋረነት አገልግሎቶችን መስጠት 31325 ታቅዶ  39177 ተፈፅሟል፡፡
  • ü   17358 አዲስ መታወቂያ አገልግሎት መስጠት ታቅዶ ለ 13725 እድሳት ተደርጓል፡፡  

11.      ከንግድ ስራችን አንጻር፡-

  • ü  2074 አዲስ የንግድ ዋና ምዝገባ ለመስጠት ታቅዶ 993 ተከናውኗል፡፡
  • ü   3004 አዲስ ንግድ ፈቃድ  ለመስጠት ታቅዶ 934 ክንውኑ 31% ለማድረስ ተችሏል፡፡
  • ü  9,099 ነጋዴዎች ንግድ ፈቃድ እድሳት ለማካሄድ ታቅዶ 3,124 ተከናውኗል፡፡  
  • ü  48,645 ኩንታል ስንዴ ለማሰራጨት ታቅዶ 12,460.31 ኩንታል ተሰራጭቷል፡፡
  • ü   55,290 ኩንታል ስኳር ለማሰራጨት ታቅዶ 42,810 ኩንታል ተሰራጭተወል፡፡
  • ü   3,092,592 ሊትር ፓልም ዘይት ለማሰራጨት ታቅዶ 2,083,196 ተከናውኗል
  • ü  በህገ ወጥ ንግድ  1.5 ሚሊዬን ሚገመት ንብረት ተወርሷል፡፡
  • ü  108 ያለንግድ ፍቃድ ሲነግዱ ተገኝተው ርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡
  • ü  40 ነጋዴዎች ያለደረሰኝ ተግኝተው ርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡
  • ü  37 ነጋዴዎች የዳቦ ግራም አጉድለው በመገኘታቸው ርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

12.      የገቢ አቅማችንን ለማሳደግ ስንመለከት፡-

  • ü  ከቀጥታ ታክስ 242,135,597.39 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 16,999,004.04 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል፡፡
  • ü   ቀጥታ ካልሆነ ታክስ 151,924,009.42 ሚሊዮን ብር ታቅዶ 23,885,222.16 ሚሊዮን ተሰብስቧል፡፡
  • ü   ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ብር 48,603,840.02 ሚሊዮን ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 1,754,521.63 ሚሊዮን መሰብሰብ ተችሏል።
  • ü  በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ከታክስና ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች 442,663,840,02 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 42,638,747.8 ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል፡፡

13.      የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር፡-

  • ü  25,506,389 ብር ግዢ ለመፈፀም ታቅዶ  4,417,222.00 ብር ግዢ ተከናውኗል፡፡  
  • ü   በግልጽ ጨረታ 21,250,000.00 ግዥ ለመፈፀም ታቅዶ  150,628,00 ተፈጽሟል፡፡
  • ü  181‚602‚613.00 ብር የውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 187‚614,891.51 ተሰብስቧል፡፡
  • ü  ከመደበኛና ካፒታል በጀት 87,601,865.40 ብር ለመጠቀም ታቅዶ 122,958,834.94 ቢሊየን ብር ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

14.      በማዘጋጃ ቤታዊ አገለግሎት ዘርፍ

  • ü  በሳምንት 2 ጊዜ 120,226 ነዋሪዎች የቤት ለቤት ደረቅ ቆሻሻ መሰብሰብ አገልግሎት ለመስጠት 91,220 ነዋሪዎች አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡
  • ü  149 ለሚሆኑ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ስለ ደረቅ ቆሻሻ አያያዝ፣ መልሶ ወደ ጥቅም መቀየርና አወጋገድ ቀጣይነት ባለው መልኩ በተጓዳኝ ትምህርት እንዲካተትና ትምህርቱ እንዲሰጥ ለማድረግ ታቅዶ ተግባራዊ ተደርጓል፡፡
  • ü  120,226 አባወራ/እማወራ በቀን የሚያመነጨውን የቆሻሻ መጠን እንዲቀንስ፣ ቆሻሻን በአይነት እንዲለይ፣ ለማህበራት እንዲያስረክብ እና የአካባቢውን ንጽህና እንዲጠበቅ የቤት ለቤት ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እንዲሰራ በየወሩ ክትትል ለማድረግ ታቅዶ 100% ተግባዊ ሆኗል፡፡
  • ü  32.92 ቶን ደረቅ ቆሻሻ ሰብስቦ ጥቅም እንዲሰጥ ለማድረግ ታቅዶ 349.11 ቶን ተሰብስቧል፡፡
  • ü  1606 / የመንገድ ፓርኮች በአዲስ ይለማሉ ተብሎ ታቅዶ 2111 ካሬ.ሜ ለምተዋል፡፡
  • ü   110378 / የመንገድ ፓርኮች በነባር እንክብካቤ ይደረግላቸዋል ተብሎ ታቅዶ 110378 / እንክብካቤ ተደርጓል፡፡
  • ü   13867 / ቁርጥራጭ አረንጓዴ  ቦታዎች በአዲሰ ይለማሉ ተብሎ ታቅዶ 13861 / ለምተዋል፡፡
  • ü  267,605 / ነባር ቁርጥራጭ አረንጓዴ ቦታዎች እንክብካቤ ይደረግላቸው ተብሎ ታቅዶ 267,605  / እንክብካቤ ተደርጓል፡፡

15.           በሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ዘርፍ፡- 


  • ü  ሴፍ ሄቨን በተባለ ድርጅት 117 የህጻናት ወላጆች በህጻናት አያያዝ ፤አስተዳደግ እና በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የወላጆች ሚና ምን መሆን እንዳለበት የግንዛቤ መድረክ  ተፈጥረዋል፡፡
  • ü  የህጻናትን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅ 38,092 ህጻናትን እና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችን ተሳትፎና ግንዛቤ ለማሳደግ ታቅዶ 29,767 ማከናወን ተችሏል፡፡
  • ü  ለህጻናት ተሳትፎ ታላቅ ሚና የሚኖራቸውን 14 የህጻናት ፓርላማን ለማጠናከር ታቅዶ 14 የህጻናት ፓርላማን ማጠናከር ተችሏል፡፡
  • ü  13 የህጻናት ክበባትን በየደረጃውና በየት/ቤቱ  ለማስፋፋትና ለማጠናር ታቅዶ 13 ክበባትን ማጠናከር ተችሏል፤ ለክበባትም በህጻናት ፖሊሲ ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
  • ü  19,425 ህጻናት የማህበረሰብ አቀፍ ድጋፍና ክብካቤ አገልግሎት እንዲያገኙ ታቅዶ 18,468 ተከናውኗል፡፡
  • ü  141 ህጻናት በመልሶ ማቀላቀል ፕሮግራም ተጠቃሚ  እንዲሆኑ ታቅዶ 60ዎቹ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
  • ü  16 ህጻናት የአደራ ቤተሰብ  አገልግሎት እንዲያገኙ ታቅዶ 7 ተከናውኗል 78 ህጻናት የጉዲፈቻ አገልግሎት እንዲያገኙ ታቅዶ  44 ተከናውኗል፡፡

16. በወጣቶችና ስፖርት ዘርፍ፡-

  • ü  17ኛው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት 9 ተግባራት 200 ነዋሪዎችን በማነቃነቅ 25 ነዋሪዎችን ተጠቃሚ በማድረግ 20 ሚሊየን ብር የሚገመት አስተዋጽኦ ማድረግ ተችሏልል፡፡
  • ü  8500 ተማሪዎች በማጠናከሪያ ትምህርት እንዲማሩ ለማድረግ ታቅዶ 6319 ተማሪዎችን ማስተማር የተቻለ ሲሆን በዚህ ተግባር 200 በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች በማስተማር ስራ መሰማራት ችለዋል፡፡ አጠቃለይ ተግባሩ በገንዘብ ሲተመንሰ 3 327 600 ብር ይገመታል፡፡
  • ü  14 ወጣት ማእከል 980 ወጣቶችን በመሰረታዊ የኮምፒዩተር ስልጠና እንዲያገኙ  ለማድረግ ታቅዶ 1015 ወጣቶች 34 አሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ተችሏል፡፡
  • ü  17000 የክ/ከተማችንን ነዋሪዎች በማነቃነቅ 33000 ችግኞችንለመትከልና ታቅዶ 161 141 ነዋሪዎችን በማነቃነቅ 165 434 የችግኝ መትከያ ጉድጓድ በመቆፈር 125189 ችግኞችን መትከል ተችሏል፡፡ አጠቃላይ የተሰራው ስራ በገንዘብ ሲተመን 4804230 ብር ይገመታል፡፡
  • ü  30000 የክ/ከተማችንን ነዋሪዎች በማነቃነቅ 1500/ ቆሻሻ ለማጽዳትታቅዶ 32,228 ነዋሪዎችን በማነቃነቅ 1422 / ቆሻሻ ማጽዳት  ተችሏል፡፡ አጠቃላይ የተሰራው ስራ በገንዘብ ሲተመን 3,228,300ብር ይገመታል፡፡
  • ü  አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ 1500 አቅመ ደካሞች የበአል መዋያ ድጋፍ ለማድረግ ታቅዶ 2487 አቅመደካሞች ዶሮ፤እንቁላል፤በግ፤ዱቄት፤ዘይት ወዘተ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ በጤና /ቤት አስተባባሪነት 100 ብር ለኩላሊት ህሙማን ማህበር መለገስ ተችሏል፡፡

17. ከቅሬታና አቤቱታ ጉዳዮች አንጻር -

  • አግባብነት ካላቸው 55 ቅሬታ፤ አቤቱታ እና ጥቆማዎች ውስጥ  31 ቅሬታና አቤቱታዎች ምላሽ አግኝተዋል፡፡
  •  በቅሬታ አቀባበልና አፈታት ላይ አሁንም ቢሆን ከነበረው የፖለቲካ አመራር ሽግሽግና የፖለቲካ ያለመረጋጋት እንዲሁም በሁሉም ደረጃ በሚገኝ የፈጻሚ አካላቱ ተሳትፎ በሚጠበቀው ደረጃ ያላደገ እና አልፎ አልፎ አሳሳቢ መሆኑ ተገምግሟል፡፡ ለአብነትም አሁንም ምላሽ በጽሁፍ የማይሰጡ፤መረጃ ሲጠየቁ የሚከለክሉ ከቢሮ የሚያስወጡ አካላትም እንዳሉ ተጠቅሷል፡፡

18.   በባህልና ቱሪዝም ዘርፍ፡-


  • ü  በልማት በመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣በፌስቲቫል፣ ውይይት ላይ በሩብ ዓመት 30000 ለማሳተፍ አቅደን 26000 ህዝብ በማሳተፍ የእቅዱን 87% ማከናወን ተችሏል፡፡
  • ü  በሃገራችን 32 ጊዜ የእየተከበረ ያለዉ የዓለም ቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ በከፍለ ከተማችን 14ቱም ወረዳ የቱሪዝም ቀንን ምክኒያት በማድረግ በእያንዳንዱ ወረዳ በተለዩ የችግኝ ተከላ ቦታዎች እንክብካቤ ማድረግ ተችሏል፡፡
  • ü   የባህል የኪነ-ጥበብ ኢንዱስትሪ ልማትና የገበያ ትስስር ማሳደግ፡- አምስት የተለያዩ  የኪነ-ጥበብ/ስነ-ጽሁፍ ምሽት መድረኮች ለማዘጋጀት ታቅዶ  5 ማድረስ ተችሏል፡፡ 
  • ü  የክፍለ ከተማ ባህል ቡድን 2 ትዉፊታዊ ሥራዎችን እንዲያቀርቡ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ተችሏል፡፡
  • ü  የንባብ ባህልን ማሳደግ፡- 5000 ህዝብ የቤተመጽሀፍት ንባብ አገልግሎት መስጠት ተችሏል፡፡
  • ü  900 ህዝብ የቤተመጽሀፍት የውሰት አገልግሎት መስጠት ተችሏል፡፡

19. ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ-


  • ü  300 ዜጎች ድጋፍ በማድረግ በአገር ውስጥ ሥራ እንዲሰማሩ ለማድረግ ታቅዶ  320 /ሴት 217/  የሚሆኑት ወደ ስራ ተሰማርተዋል፡፡
  • ü   በመደበኛ የተፈጠሩ የሥራ ዕድሎች 259 ሲሆኑ ለጎዳና ተዳዳሪዎች የተፈጠረው የሥራ ዕድል 62 ነው፡፡
  • ü  594 በቀጥታ ድጋፍ ዙሪያ በጋራ ከልማታዊ ሴፍቲኔት /ቤት ጋር በመሆን ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

20.           የአካባቢ ጥበቃና ብዝሀ ህይወት፡-

 2011 . የክረምት መርሃ ግብር በጉድጓድ ቆፋሮና በችግኝ ተከላ 200 ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ 352 ወጣትና ሴቶች የስራ ዕድል በመፍጠር 1,075,795 ብር ገቢ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ 2011 . የክረምት መርሃ ግብር በህዝብ ተሳትፎና በጉልበት ሰራተኛ በሶስት ዙር 552,480 ችግኞች በፈረንሳይ፣በሚሊኒየምና በኮተቤ ደን ክልል ውስጥ እንዲተከል ተደርጓል፡፡ በዚህም 441.9 ሄክታር በላይ በእፅዋት እንዲሸፈን ተደርጓል፡፡ 4344 ሄክታር በደን የተሸፈነ የአረንጓዴ ቦታዎች ክትትል የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡ በየካ አባዶ የጋራ መኖሪያ ቤት በተሰራው የድምጽ ልኬት መሰረት ከተቋማቸው በሚፈጠረው የድምጽ ብክለት በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ማስተካከያ ማድግ ባልቻሉት 10 የንግድ ተቋማት ላይ በመመሪያው መሰረት እርምጃ መውሰድ ተችሏል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ

በዜሮ ዓመት የወጣ ክፍት የስራ ማስታወቂያ

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት