ዴሞክራሲ
ዴሞክራሲ
ዴሞክራሲ የፖለቲካ ሥርዓት ሲሆን ትርጓሜውም ሕዝባዊ መንግስት ማለት ነው። በሌላ አባባል ዲሞክራሲ ማለት ህዝብ የሚያስተዳድረውን አካል ያለምንም ተፅዕኖ ከመካከሉ መርጦ ሥልጣን የሚሰጥበት ሥርዓት ነው።
ዲሞክራሲ ሁለት ነው
|
ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆነ
|
ዲሞክራሲ በተጠነሰሰበት ጥንታዊት ግሪክ ፣ ሰዎች ይኖሩ የነበረበት መሠረታዊ የፖለቲካ አሃድ (ዩኒት) ፣ ከተማዊ መንግስት ይባላል። ይህ በአሁን ዘመን ካለው አገር ወይንም ብሔራዊ መንግስት ይለያል። ከተማዊ መንግስታት፣ ለምሳሌ አቴና እንደ ከተማ አስተዳደርነቱ ፣ በቆዳ ስፋት አንስተኛ ስለነበር የዘመኑ ዲሞክራሲ በቀጥተኛ ተሳትፎ (በስብሰባ) ላይ የተመሰረተ ነበር። ነገር ግን ይህ ዓይነት አሰራር ከ፲፯ኛው (17) ክፍለ ዘመን በኋላ ለተነሱት በንፅፅር ግዙፍ ለሆኑት ብሔረ መንግስታት እማይቻል ስለነበር (ማለት ከአገሪቱ ግዙፍ የቆዳ ስፋት አንጻር ሁሉን ዜጋ በየሳምንቱ ለስብሰባ መጥራት ስለማይቻል) በእንግሊዝ አገር ፓርላማ የተባለ አዲስ ሥርዓት ተፈጠረ። ይህም ማለት ሕዝቡ ተወካዮቹን (የፓርላማ ዓባላትን) ይመርጣል፤ ተመራጮችም መንግሥትን ይመሠርታሉ። ይህ ዓይነት ሥርዓት (ቀጥተኛ ያልሆነ ዴሞክራሲ) በመባል ይታዎቃል። በአሁኑ ሰአት አብዛሃኛዎቹ የአለም ሃገራት የሚጠቀሙበት የመንግስት መዋቅር ነው።
ዜግነትና ዴሞክራሲ
|
አንድ ሥርዓት ዲሞክራሲያዊ፣ በሌላ አነጋገግር ከሕዝብ ወይም በሕዝብ የቆመ ነው ከተባለ፣ ሕዝብ ማለት እዚህ ላይ ምንድን ነው? አብዛኛውን ጊዜ ሕዝብ ማለት ዜጋ ማለትን ሲዎክል፣ እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን ድረስ አብዛኞች ዲሞክራሲያዊ ሃገሮች ዜግነትን ትንሽ ለሆነ የህብረተሰብ ክፍል (ሴቶችን፣ ድሆችን፣ ዘሮችን ያገለሉ) ብቻ ያድሉ ነበር። እነዚህ ትንሽ ክፍሎች ብቻ እሚሳተፉበት ዴሞክራሲ በአሁኑ ዘመን ተቀባይነትን ያጣ ነው። ባሁኑ ዘመን፣ ዲሞክራሲ ማለት ብዙኃኑ ኅብረተሰብ መንግሥት የማዋቀር መብት አለው። የጥቂቶች መብት ደግሞ በህግ የተጠበቀ ነው።
ሥርዓተ ሕዝብ፣ ሥርዓተ ልሂቅ፣ ሥርዓተ ጥቂት
|
ፖለቲካዊ ዜግነት ሕጻናትን እንደማይጨምር አሁን ድረስ አብዛኞች ሃገራት የሚሰሩበት ነው። ይሁንና፣ በዚህ መንገድ አላግባብ ሌሎችም የሕዝብ አካላት እየተገለሉ ሄደው፣ ዴሞክራሲው ወደ ሌላ ዓይነት ሥርዓት ሊቀየር ይችላል። ለምሳሌ በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ የተከበሩ ሰዎች ብቻ እሚሳተፉበት ሥርዓት ሲፈጠር ሥርዓተ ልሂቅ ወይንም አሪስቶክራሲ ይባላል። በሆነ አጋጣሚ ዕድል አግኝተው ጥቂት ቡድኖች ብቻ በማህበረሰቡ ላይ በሚተላለፉ ውሳኔዎች ሲሳተፉ ሥርዓተ ጥቂት ወይንም ኦሊጋርኪ ይባላል። ይህን ሁኔታ ለማዎቅ አንድ አንድ ጊዜ አስቸጋሪ ይሆናል ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ዴሞክራሲያዊ በሆነ ሥርዓት ሳይቀር፣ ጊዜ አግኝተው በፖለቲካው የሚሳተፉ ግለሰቦች ከአጠቃላይ ዜጋ ጥቂት ስለሆኑ። ይሁንና በዲሞክራሲ፣ የመሳተፍ መብቱ ለሁሉም ዜጋ ምንጊዜም ያለ ነው፣ ይጠቀሙበት አይጠቀሙበት።
ዴሞክራሲ ለምን ተፈለገ?
|
ሥልታዊ ምክንያት
|
ሥነ ዕውቀታዊ ምክንያት
|
ዴሞክራሲ አብዛኛውን ሕዝብ በውሳኔ አስጣጥ ላይ ስለሚያካፍል፣ ከሌሎች የፓለቲካ ሥርዓቶች በበለጠ ሥለ ሕዝቡ ጉዳይ ያዎቀ ሆኖ ይገኛል። በውሳኔ አሰጣጥ የሚካፈለው ሕዝብ መብዛት በሌላ ጎን ትክክለኛ ውሳኔ ላይ ለመድረስ እሚደረገውን ስራ ያግዛል፣ ተሳታፊዎችም ስለ ጉዳዮች የበለጠ የተተቸና የተብራራ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ይረዳል።
የዜጎችን ባሕርይ የማሻሻል ምክንያት
|
በዴሞክራሲ ሥርዓት ያሉ ሰዎች በውሳኔዎች ላይ ስለሚሳተፉ፤ ከሌሎች ሥርዓት ሰዎች በተለየ እራሳቸውን ችለው እንዲያስቡ፣ በሃሳባቸው ምክንያታዊ እንዲሆኑ እና የሌሎችን መብቶች ግምት ውስጥ እንዲያስገቡ ስለሚገደዱ በሥነ ምግባር እንዲሻሻሉ ይሆናሉ።
በዴሞክራሲ ላይ የተነሱ ትችቶች
|
ፕላቶ የሥርዓተ ልሂቃን ዓይነት መንግስት ደጋፊ ስለነበር ዲሞክራሲን ከዚህ አቋሙ ተነስቶ ለመንቀፍ ሞክሯል። በእርሱ አስተሳሰብ በዲሞክራሲ ሥር ዓት ወደ ሥልጣን ላይ መውጣት እሚችሉት የምርጫ ሥር ዓቱን በማጭበርበር ወይንም በብልጥ ንግግር እና ስራ ሰውን በማታለል የተካኑ ሰዎች ይሆናሉ። ምርጫን እሚያሸንፉ ሰዎች ደግሞ የግዴታ መንግስታዊ ኣስተዳደር ላይ ብቁ ሆነው ስለማይገኙ፣ ዴሞክራሲ መንግስትን ለንደዚህ ያለ ግሽበት ይዳርጋል ይላል።
Comments
Post a Comment