ኑዛዜ በኢትዮጵያ ህግ 

ኑዛዜ በኢትዮጵያ ህግ 

ስለ ኢትዮጵያ የኑዛዜ ህግ ማወቅ ይፈልጋሉ; እንግዲያውስ ከዚህ በታች የተጻፈውን ጽሁፍ ስለ ኑዛዜ ምንነት፣ አይነቶች እንዲሁም ኑዛዜ ጸንቶ የሚቆይበትን ጊዜና ማን ኑዛዜ መኖሩን ማረጋገጥ እንዳለበት በዝርዝር ያትታል፡፡ መልካም ንባብ እንመኝልዎታለን፡፡

የኢትዮጵያ ፍትሐብሄር ህግ አንቀጽ 857 እና ተከታዩቹ አንቀጾች እንደሚያስቀምጡት ኑዛዜ ማለት ጥብቅ የሆነና ሟቹ ራሱ የሚፈጽመው ሥራ ነው፡፡ ማንኛውም ሰው ለሌላ ሰው በስሙ አንድ ኑዛዜ እንዲያደርግ፣ እንዲለውጥ ወይም እንዲሽር ስልጣን ሊሰጠው አይችልም፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሟቹ ኑዛዜውን የተናዘዘው /ያደረገው/ በሌላ ሰው አስገዳጅነት የሆነ እንደሆነ ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል፡፡

የፍታብሄር ህጋችን አንቀጽ 858 ኑዛዜን በጋራ ማድረግ እንደማይቻል ይደነግጋል፡፡ ሰለሆም የተለያዩ ሰዎች/ብዙ/ ሰዎች በአንድ ወረቀት ላይ አንድ ብቻ የሆነ ኑዛዜ የተናዘዙት እንደሆነ ኑዛዜው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በሌላ አባባል ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል፡፡ አንድ ሰው ኑዛዜ ሲጽፍ/ሲያደርግ የኑዛዜው ቃል በሚበቃ እኳኋን ተጠቃሚውን ወይም ጉዳዩን ካለመለከተ ፈራሽ ይሆናል፡፡ የኑዛዜው አፈፃፀም የማይቻል እንደሆነ እንደዚሁ ፈራሽ ይሆናል፡፡


በኢትዮጵያ ፍታብሄር ህግ አንቀጽ 880 መሰረትም ሦስት አይነት የኑዛዜ ፎርሞች አሉ፡፡ እነዚህም

ሀ. በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ

ለ. በተናዛዡ ጽሁፍ የሚደረግ ኑዛዜ

ሐ. በቃል የሚደረግ ኑዛዜ

***************************************************************************

ሀ. በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ

በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡ እራሱ ወይም በተናዛዡ ተናጋሪነት በሌላ ሰው ሊጻፍ ይችላል፡፡ ነገር ግን ከተፃፈ በኋላ በተናዛዡ በአራት ምስክሮች ፊት ካልተነበበና ይህም ስርአት/ፎርማሊቴ መፈፀሙንና የተፃፈበትን ቀን የሚያመለክት ካልሆነ በቀር በተጨማሪም ተናዛዡና ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ወዲያውኑ ፊርማቸውን ወይም ያውራጣት ምልክታቸውን ካላደረጉ በቀር ፊራሽ ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ አይነት ኑዛዜ ውስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦች ካልተሟሉ ኑዛዜው ፈራሽ ነው፡፡ ነጥቦቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

  • በግልጽ በሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዙ እራሱ ወይም በተናዛዡ እራሱ ወይም በተናዛዡ ተናጋሪነት በሌላ ሰው መጻፍ አለበት፣ 
  • ከተፃፈ በኋላ በተናዛዡና በአራት ምስክሮች ፊት መነበብ አለበት፣ 
  • ኑዛዜው መነበቡን ወይም ይህም አይነት ስርአት ፎርማሊቴ መፈፀሙን መግለጽ አለበት፣ 
  • የተፃፈበትን ቀን ማመልከት አለበት፣ 
  • አራት ምስክሮች መገኘት አለባቸው፣ 
  • ተናዛዡና ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ወዲያውኑ ፊርማቸውን ወይም ያውራ ጣት ምልክታቸውን ማድረግ አለባቸው፣ 
  • ሌሎች ውልን በተመለከተ የተቀመጡት የፈቃድ ድንጋጌዎችም ሊሟሉ የሚገቡ ነጥቦች፣ 
  • ከዚህ ውስጥ አንድ ወይም ከአንድ በላይ ነጥቦች ከተጓደሉ ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል፡፡


ሐ. የቃልኑዛዜ


የቃል ኑዛዜ ማለት አንድ ሰው የሞቱ መቃረብ ተስምቶት የመጨረሻ ፈቃድ ቃሎቹን በሁለት ምስክሮች ፊት የሚሰጥበት የኑዛዜ አይነት ነው፡፡ የዚህ አይነቱን ኑዛዜ ለመስማት የሚጠሩት ምስክሮች ለአካለመጠን የደረሱና በፍርድ ወይም በህግ  ያልተከለከሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተናዛዡ በዚህ የቃል ኑዛዜ ላይ  እንዲናዘዝ የሚጠበቀው ሰለቀብሩ ስነስርአት የሉትን ትዕዛዞች ከአምስት መቶ ብር በላይ ያልሆኑ የተለያዩ ስጦታዎችን ለተለያዩ ሰዎች መናዘዝ እና ለአካለመጠን ያልደረሱ ልጆች ካሉት እነሱ በሞግዚትነት የሚያስተዳድራቸውን ሰው በተመለከተ ውሣኔዎችን ለመስጠት ይችላል፡፡ በቃል የሚደረግ ኑዛዜ ከተደረገበት ከሦስት ወር በኋላ ተናዛዡ በዚህ ጊዜ ውስጥ በህይወት ያለ ከሆነ ውድቅ ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ አይነት ኑዛዜ ውስጥ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ነጥቦች ካልተሟሉ ኑዛዜው ፈራሽ ነው፡፡ ነጥቦቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

  • በሁለት ምስክሮች ፊት መስጠት አለበት፣
  • ተናዛዡ በዚህ የቃል ኑዛዜ ላይ እንዲናዘዝ የሚጠበቀው ስለቀብሩ ስነሰርአት ያሉትን ትዕዛዞች ከአምስት መቶ ብር በላይ ያልሆኑ የተለያዩ ስጦታዎችን ለተለያዩ ሰዎች መናዘዝ እና ለአካለመጠን ያልደረሱ ልጆች ካሉት እነሱን በሞግዚትነት የሚያስተዳድራቸውን ሰው በተመለከተ ውሣኔዎችን መስጠት ብቻ መሆን አለበት፡፡
  • ተፈጻሚነቱ ተናዛዡ በህይወት ባለበት ሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ ነው፣
  • ከነዚህ ውስጥ አንዱ ወይም ከአንድ በላይ ነጥቦች ከተጓደሉ ኑዛዜው ፈራሽ ይሆናል፡፡


ኑዛዜ ስለመኖሩ ማስረዳት


  • በኑዛዜው የሰፈረውን ቃልና ኑዛዜ መኖሩን ማስረዳት ያለበት ሰው በዚሁ ኑዛዜ ተጠቃሚነኝ የሚለው ሰው ነው፡፡
  • ተናዛዡ ኑዛዜዎቹ ዋጋ ያላቸው እንዲሆኑ በሚያስፈልገው ፎርም ዓይነት ግልጽ አድርጎ በማስታወቅ ኑዛዜውን የሻረ እንደሆነ ኑዛዜው በጠቅላላው አኳኋን የሚሻር ይሆናል፡፡
  • ተናዛዡ እንዲሁ በሆነ ፎርም ከአንድ የኑዛዜ የውል ቃል ጋራ አብሮ ሊፈፀም የማይቻል አንድ ውሣኔ ያደረግ እንደሆነ ኑዛዜው በከፊል የሚሻር ይሆናል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የደመወዝ ስኬል አፈጻጸም መመሪያ

በዜሮ ዓመት የወጣ ክፍት የስራ ማስታወቂያ

የነጥብ ስራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን ጥናት