ፅዱ አዲስ አበባ ለአዲስ አመት
- 'ፅዱ አዲስ አበባ ለአዲስ ዓመት' በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑን የየካ ክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት አስታወቀ::
- ህብረተሰቡ ከበአል ጋር ተያይዞ የሚፈጠረውን ቆሻሻ በአግባቡ ማስወገድ እንዳለበት ጥሪ ቀርቧል::
==============================================
"ፅዱ አዲስ አበባ ለአዲስ" አመት በሚል መሪ ቃል የፅዳት ዘመቻ እየተደረገ መሆኑን የየካ ክፍለ ስራ አስወቀ:: የፅዳት መርሀ ግብሩ ጳጉሜ 1 መጀመሩንና እስከ መስከረም 4 እንደሚቆይ ተገልፇል::
የከፍለ ከተማው ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወሰኔ በየነ ከማህበራዊ ሚዲያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ክፍለ ከተማችን ለስራና ለኑሮ ምቹና ማራኪ ለማድረግ በሁሉም ወረዳዎች : ቀጣናዎችና መንደሮች እንዲሁም ተቋማት ቆሻሻ ያለአግባብ እንዳይጣል ለማድረግ የሚያስችል ንቅናቄ መሆኑን ገልፀዋል::
አሮጌ ነገራችንን አፅድተን አዲሱን አመት በአዲስ መንፈስ መቀበል አለብን ያሉት ወ/ሮ ወሰኔ ህብረተሰቡ የአካባቢውን 50 ሜትር ራዲየስ እንዲያፀዳ : በአልን ተከትሎ የሚፈጠረውን ቆሻሻ በአግባቡ እንዲያስወግድና ከመንግስት ጉትጎታ እና ዘመቻ ወጥቶ ፅዳትን ባህሉ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል::
በትምህርት ቤቶች : በሆስፒታሎችና የሀይማኖት ተቋማት ዘመቻው መጀመሩን ጠቅሰው ከክረምት ወደ በጋ ሽግግር የሚደረግበት ወቅትም በመሆኑ የክፍለ ከተማው ህዝብ ራሱን ከተላላፊ በሽታዎች እንዲጠብቅ ሀላፊዋ አሳስበዋል::
ተቋሙ በቀጣይ በጀት አመት የህብረተሰቡን የፅዳት ባህል ማሳደግ እና ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም የክፍለ ከተማውን ገፅታ መገንባት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ወ/ሮ ወሰኔ ተናግረዋል::
Comments
Post a Comment