ለ2012 የስራ ዘመን 1.9 ቢሊዮን ብር በጀት ተይዟል
ክፍለ ከተማው ለ 2012 የስራ ዘመን 1 ቢሊየን 942 ሚሊዮን 901 ሽህ 384 ብር በጀት መመደቡን አስታወቀ :: ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ የየካ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ፅ / ቤት የ 2012 የስራ ዘመን በጀትን አስመልክቶ ከምክር ቤት ዘርፍ ኮሚቴዎች ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት እንደገለፀው ለአስተዳደሩ የስራ ማስኬጃና ካፒታል በጀት 1.9 ቢሊዮን ብር መመደቡን አስታውቋል :: ከተመደበው በጀት 90% የሚሆነው ከገቢና አገልግሎት ክፍያ ከሚሰበሰብ ገቢ የሚሰበሰብ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በ 2012 በጀት አመት 977.9 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱ ታውቋል :: ለማህበራዊ ዘርፍ ተቋማት ማለትም ለጤናና ትምህርት የበጀት አፈፃፀማቸውንና የማስፈፀም አቅማቸውን መሰረት ያደረገ ከፍተኛ በጀት መያዙ ታውቋል :: ከክፍለ ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ክፍት የስራ መደቦች 50 ሚሊዮን እንዲሁም 20 ሚሊዮን መጠባበቂያ በጀት መያዙንም ፅ / ቤቱ አስታውቋል :: በ 2012 የተያዘው በጀት ከአምናው ተመሳሳይ ዘመን ጋር ሲነፃፀር የ 334238612 ወይም የ 20.76% ብልጫ እንዳለው ተጠቅሷል :: የምክር ቤት ዘርፍ ኮሚቴዎች በበኩላቸው በገቢ ግብር መሰብሰብ ተግባር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ አሳስበዋል ::