ክፍት የስራ መደቦች ለስራ ፈላጊ የገፃችን ተከታታዮች ታህሳስ 2/2012 የወጡ የኢትዮጵያ ብዝሐ ህይወት ኢንስቲቲዩት 89 ክፍት ቦታዎች ( 49- ቦታዎች 0 ልምድ , 40- ልምድ የሚጠይቁ ) የመመዝገቢያ ቦታ ቀበና ኬንያ ኢንባሲ ጎን የመመዝገቢያ ቀን ከትላንት ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፌደራል ስፖርት ኮሚሽን (Federal Sport Commission ) 15 ክፍት መደቦች ( 6- ቦታዎች 0 ዓመት , 9- ቦታዎች በልምድ የመመዝገቢያ ቦታ መስቀል አደባባይ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት የመመዝገቢያ ጊዜ ከትላንት ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ( Ethiopian Ministry of Revenues ) 10 ቦታዎች ( with EXP): የመመዝገቢያ ቦታ መገናኛ ዋናው መስሪያ ቤት ( ከትላንት ጀምሮ ባሉት 6 ተከታታይ የስራ ቀናት ለበለጠ መረጃ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታህሳስ 2/2012 እትም መመልከት ይቻላል :: የመረጃ ምንጫችን ethiopage.com ነው yekasec.blogspot.com የጡመራ ገፃችን ለእናንተ አዳዲስ መረጃዎችን ያደርሳል ::
Posts
Showing posts from December, 2019
የኩላሊት ጠጠር
- Get link
- X
- Other Apps
የኩላሊት ጠጠር ምንድን ነው? -------------------- ሰላም ጤና ይስጥልን ውድ የየካ ማህበራዊ ሚዲያ ገፅ ተከታዮች ዋናው ጤና በሚል አምድ የተለያዩ የጤና ጉዳዮችን የሚዳስሱ አርዕስት በመምረጥና መረጃ በማሰባሰብ ወደናንተ የምናደርስ ይሆናል:: ለዛሬ ስለ ኩላሊት ጠጠረ ምንነት: መንስኤው: ምልክቱ: ህክምናውና መከላከያ ዘዴው የሚዳስስ ፁሁፍ መርጠንሎታል መልካም ንባብ ይሁንልዎ! የኩላሊት ጠጠር የሚባለው በኩላሊት ውስጥ የጠጣር ነገሮች መጋገር ወይም መሰብሰብ ሲሆን የጠጣር ነገሮቹም ምንጭ በሽንት ውስጥ የሚገኙ የምግብ ንጥረ ነገሮች ናቸው:: የኩላሊት ጠጠሮች በተለያየ መልኩ ሊከፈሉ ይችላሉ፤ ከነዚህም ውስጥ በሚገኙበት ቦታ ማለትም በሽንት ትቦና በሽንት ፊኛ፤ በጠጠሮቹ ውስጥ በሚገኙ ማእድናት ማለትም ካልሺየም፣ማግኒዢየምና አሞኒየም ፎስፌት፤ የሽንት አሲድ ወይም ሌላ ማእድናት የያዙ በማለት ሊሆን ይችላል። የኩላሊት ጠጠር የከፍተኛ ህመም ምንጭ ሲሆን በአብዛኛው ወንዶችን ያጠቃል፤ ወንዶች በአብዛኛው የኩላሊት ጠጠር ህመም ከ30-40 ባለው እድሜያቸው ሲጀምራቸው ሴቶች ላይ ግን ዘግይቶ ሊከሰት ይችላል። የኩላሊት ጠጠሮች አብዛኛውን ጊዜ ምንም የህመም ስሜትና ጉዳት ሳያስከትሉ በሽንት መስመር ውስጥ አልፈው ከሰውነት ይወገዳሉ:: ነገር ግን ጠጠሮቹ በመጠን ከጨመሩ ማለትም ከ3 ሚ.ሜ አካባቢ ከደረሱ፣ የሽንት ትቦን ሊዘጉ ይችላሉ:: የሽንት ትቦ በጠጠር መዘጋት ሽንት በቀላሉ እንዳይተላለፍ (ፓስቴርናል አዞቶሚያ) ብሎም ሽንት ወደ ኋላ በመመለስና በኩላሊት ውስጥ በመከማቸት (ሃይድሮኔፕሮሊስ) ጉዳት ሊያደርስ ይችላል:: ይሄ የጤና ችግር (ሃይድሮኔፕሮሊስ) ከታችኛው የጎድን አጥንት አንስቶ እስከ የዳሌ አጥንት ድረስ ባለው ቦታ፣ በብሽሽትና በታችኛው የምግብ መ...
አዋጅ ቁጥር 1064/2010
- Get link
- X
- Other Apps
የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 Federal Civil Servants Proclamation 1064-2017 በመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚካሄደውን የምልመላና መረጣ ሥርዓትን በመሰረታዊነት በመለወጥና በአገር አቀፍ ደረጃ የሙያና የሥራ ብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት በመዘርጋት፣ እንዲሁም የመንግስት ሠራተኛው በዚህ ሥርዓት ውስጥ እንዲያልፍ በማድረግ ብዝሀነትን ያረጋገጠና ሀገሪቱ እያስመዘገበች ያለችውን እድገት ለማስቀጠል የሚያስችል ፐብሊክ ሰርቪስ ለመገንባትና የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም በሰው ሃብት ሥራ አመራር ረገድ ያመጣቸውን ውጤቶች ለማጎልበትና ለማስቀጠል የሚያስችል ሕግ ማውጣት በማስፈለጉ፤ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ያሉ ሰራተኞችን ወጥነት ባለው መልኩ ለመምራትና እውቀታቸውንና ችሎታቸውን በተገቢው ሁኔታ ለመጠቀም የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ያሏቸውን ሠራተኞች በማቆየትና አዳዲስ ሰራተኞችን በመሳብ ተወዳዳሪ ለመሆን እንዲችሉ የተሻሻሉ የሥራ ሁኔታዎችን ማመቻቸት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጅዋል፡፡ ክፍል አንድ ጠቅላላ አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ትርጓሜ የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፣ 1/ “የመንግሥት ሠራተኛ” ማለት በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ውስጥ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው ነው፤ ሆኖም የሚከተሉትን አይጨምርም፤ ሀ) ሚኒስትር ዴኤታዎችን፣ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችን፣ ...